Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 14:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የግብጽ ሠራዊት በፈረሶችና በሠረገላዎች ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ ተከታተላቸው፤ በቀይ ባሕር ፊት ለፊት ባሉት በፒሃሒሮት በባዓልጸፎን አጠገብ በሰፈሩበት ቦታ ደረሱባቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ግብጻውያን፣ ይኸውም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገላዎች፣ ፈረሰኞችና እግረኞች ሁሉ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው፤ በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ በፊሀሒሮት ሰፍረው ሳሉ ደረሱባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ግብፃውያንም የፈርዖን ፈረሶችና ሰረገሎች ፈረሰኞቹም ሠራዊቱም ሁሉ፥ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ በበዓልጽፎን ፊት ለፊት ባለው በፒሃሒሮት ሰፍረው አገኙአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም፥ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ በባ​ሕሩ ዳር በብ​ኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መን​ደር አን​ጻ​ርም ሰፍ​ረው አገ​ኙ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ግብፃውያንም የፈርዖን ፈረሶች ሰረገሎቹም ፈረሰኞቹም ሠራዊቱም ሁሉ፥ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ ዳር በበኣልዛፎን ፊት ለፊት ባለው በፊሀሒሮት አጠገብ ሰፍረው አገኙአቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 14:9
5 交叉引用  

ስለዚህ ይህን በማድረግ ፈንታ ወደ ቀይ ባሕር በሚያመራው በረሓ፥ ዘወርዋራ በሆነ መንገድ መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ሆነው ከግብጽ ወጡ።


“እስራኤላውያን ተመልሰው፥ በሚግዶልና በቀይ ባሕር መካከል ባለው ፒሃሒሮት ፊት ለፊት በባዓልጸፎን አጠገብ እንዲሰፍሩ ንገራቸው።


‘ጠላትማ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ሀብታቸውንም እካፈላለሁ፤ የፈለግኹትንም እወስዳለሁ፤ ሰይፌንም መዝዤ አጠፋቸዋለሁ’ ብሎ ነበር፤


ከኤታም ተነሥተው በባዓልጸፎን በስተምሥራቅ ወደ ፒሃሒሮት በመመለስ በሚግዶል ፊት ለፊት ሰፈሩ፤


የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ወደ ባሕር ደረሱ፤ ግብጻውያንም በሠረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ባሳደዱአቸው ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告