ዘፀአት 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 የግብጽ ንጉሥ ልቡን አደንድኖ እልኸኛ በመሆን አለቃችሁም ባለ ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የሰውንም ሆነ የእንስሶችን በኲር ሁሉ ገደለ፤ በኲር ሆኖ የተወለደውን ወንድ እንስሳ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርበው በዚህ ምክንያት ነው፤ በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ልጆቻችንን ግን እንዋጃቸዋለን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ፈርዖን እኛን አልለቅም ብሎ ልቡን ባደነደነ ጊዜ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ በኵር ሆኖ በግብጽ የተወለደውን ሁሉ እግዚአብሔር ገደለው። እንግዲህ በመጀመሪያ የእናቱን ማሕፀን የከፈተውን ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የምሠዋውና የልጆቼ በኵር ሆኖ የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ የምዋጀው በዚህ ምክንያት ነው።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ፈርዖን እንዳይለቀን ልቡን ባጸና ጊዜ ጌታ ከሰው በኩር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኩር ድረስ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ ገደለ፤ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለጌታ እሠዋለሁ፥ ነገር ግን የልጆቼን በኩር ሁሉ እዋጃለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ፈርዖንም እኛን ለመልቀቅ እንቢ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኵር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ፤ ነገር ግን የልጆችን በኵር ሁሉ እዋጃለሁ።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ፈርዖንም እንዳይሰድደን ልቡን ባጸና ጊዜ እግዚአብሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኵር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ፤ ነገር ግን የልጆቼን በኵር ሁሉ እዋጃለሁ። 参见章节 |