ዘፀአት 12:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 በዚያኑ ሌሊት ንጉሡና መኳንንቱ፥ መላውም የግብጽ ሕዝብ ሁሉ ከእንቅልፋቸው ነቁ፤ ወንድ ልጅ ያልሞተበት አንድ ቤት እንኳ ስላልነበረ በግብጽ ምድር ሁሉ ታላቅ የለቅሶ ጩኸት አስተጋባ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ፈርዖን፣ ሹማምቱና የግብጽ ሕዝብ በሙሉ ሌሊቱን ከመኝታቸው ተነሡ፤ እነሆ በመላዪቱ ግብጽ ልቅሶና ዋይታ ነበር፤ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት አልነበረምና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ፈርዖን፥ አገልጋዮቹ ሁሉና ግብጽ ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብጽ ምድር ታላቅ ልቅሶ ሆነ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ፈርዖንም፥ ሹሞቹም ሁሉ፥ ግብፃውያንም ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብፅ ምድር ሁሉ ታላቅ ልቅሶ ሆነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ፈርዖንም ባሪያዎቹም ሁሉ ግብፃውያንም ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብፅ ምድር ታላቅ ልቅሶ ሆነ። 参见章节 |