6 አይሁድ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ብቻ እንኳ አምስት መቶ ሰው ፈጁ።
6 አይሁድ በሱሳ ግንብ ዐምስት መቶ ሰው ገደሉ፤ አጠፉም።
6 አይሁድም በሱሳ ግንብ አምስት መቶ ያህል ሰዎች ገደሉ አጠፉም።
በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።
በዚህ ዐይነት አይሁድ በጠላቶቻቸው ላይ የፈለጉትን ለማድረግ ቻሉ፤ በሰይፍ እያጠቁም ጨፈጨፉአቸው።
ከነዚህም ውስጥ ፓርሻንዳታ፥ ዳልፎን፥ አስፓታ፥ ፖራታ፥ አዳልያ፥ አሪዳታ፥ ፓርማሽታ፥ አሪሳይ፥ አሪዳይና ዋይዛታ ተብለው የሚጠሩት የሃመዳታ ልጅ የሆነው የአይሁድ ጠላት የሃማን ልጆች ይገኙባቸዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን የንብረት ዝርፊያ አላካሄዱም።
ልጆቹ ቢበዙ በጦርነት ያልቃሉ፤ ዘሮቹም ምግብ አጥተው ይራባሉ።