አስቴር 9:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ከዚህም ጋር ከአሁን በፊት ለጾምና ለሐዘን ደንብ አውጥተው በነበረው ዐይነት እነዚህን የፑሪም ዕለቶች እነርሱ ራሳቸውም ሆኑ ወደፊት የሚነሡት ዘሮቻቸው በየዓመቱ በማክበር ይጠብቁአቸው ዘንድ ይጠይቃል፤ ይህም ንግሥት አስቴርና መርዶክዮስ በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ሁለቱም ያስተላለፉት ትእዛዝ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 የላከውም አይሁዳዊው መርዶክዮስና ንግሥት አስቴር ባወጁላቸውና እንደዚሁም የጾሙንና የሰቈቃውን ጊዜ በሚመለከት ለራሳቸውና ለዘራቸው ባጸኑት ውሳኔ መሠረት እነዚህ የፉሪም ቀኖች በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲከበሩ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 እነዚህንም የፉሪም ቀኖች፥ አይሁዳዊው መርዶክዮስና ንግሥቲቱ አስቴር እንዳዘዙ፥ ለራሳቸውና ለዘራቸውም የጾማቸውንና የልቅሶአቸውን ነገር ለማክበር እንደ ተቀበሉ፥ በየጊዜያቸው ያጸኑ ዘንድ ጻፉ። 参见章节 |