Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እነዚህ የፑሪም ቀኖች በየትውልዱ፥ በየቤተሰቡ፥ በየሀገሩና በየከተማው መከበር እንዳለባቸው ተወሰነ፤ እነዚህም ቀኞች ሳይከበሩ መቅረት የለባቸውም፤ ከትውልዱም መካከል መታሰቢያነታቸው መቋረጥ የለበትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እነዚህም ቀኖች በእያንዳንዱ ትውልድ፣ በእያንዳንዱ ቤተ ሰብ፣ በእያንዳንዱ አውራጃና በእያንዳንዱ ከተማ መታሰብና መከበር ይኖርባቸዋል፤ ይኸውም እነዚህ የፉሪም ቀኖች በአይሁድ ዘንድ ሳይከበሩ እንዳይቀሩ፤ መታሰቢያቸውም ከዘሮቻቸው መካከል እንዳይደመሰስ ነው።

参见章节 复制




አስቴር 9:28
9 交叉引用  

አይሁድ ለራሳቸው፥ ለዘሮቻቸው አይሁዳዊ መሆን ለሚፈልግ ሁሉ ቋሚ ደንብ አደረጉ፤ ይኸውም በየዓመቱ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ መርዶክዮስ በሰጠው መመሪያ መሠረት እነዚህ ሁለት ቀኖች ባለማቋረጥ ይከበራሉ።


ከዚህም ሁሉ በኋላ የአቢኀይል ልጅ ንግሥት አስቴር ከመርዶክዮስ ጋር በመተባበር ስለ ፑሪም፥ መርዶክዮስ ቀደም ሲል የላከውን ደብዳቤ በማጠናከር ያላትን ሥልጣን የሚገልጥ ትእዛዝ ያለበት ደብዳቤ ጽፋ ላከች።


ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! ቸርነቱንም አትርሺ!


አንድ ትውልድ የአንተን ሥራ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋል፤ ድንቅ ሥራህንም ይገልጣል።


መላውን የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣሁት በዚህ ቀን ስለ ሆነ ይህን የቂጣ በዓል ትጠብቃላችሁ፤ በሚመጡትም ዘመናት ሁሉ ይህን በዓል ማክበር ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።


ዘውዱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሔሌም ለተባለ ለሔልዳይ፥ ለጦቢያ፥ ለይዳዕያና ለሰፎንያስ ልጅ ሔን ለኢዮስያስ ክብር መታሰቢያ ሆኖ ይቀመጣል።”


እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትነግሩአቸዋላችሁ፦ ‘የአምላካችሁ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚሻገርበት ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መውረዱን አቆመ፤ ስለዚህም እነዚህ ድንጋዮች በዚህ ስፍራ የተደረገውን ሁሉ ለዘለቄታው ለእስራኤል ሕዝብ የሚያስታውሱ መታሰቢያዎች ናቸው።’ ”


跟着我们:

广告


广告