Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አይሁድ ለራሳቸው፥ ለዘሮቻቸው አይሁዳዊ መሆን ለሚፈልግ ሁሉ ቋሚ ደንብ አደረጉ፤ ይኸውም በየዓመቱ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ መርዶክዮስ በሰጠው መመሪያ መሠረት እነዚህ ሁለት ቀኖች ባለማቋረጥ ይከበራሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አይሁድ በታዘዘውና በተወሰነው ጊዜ እነርሱና ዘሮቻቸው፣ እነርሱን የተጠጓቸውም ሁሉ እነዚህን ሁለት ቀኖች በየዓመቱ ባለማቋረጥ እንዲያከብሩ ሥርዐት አድርገው ራሳቸው ወሰኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27-28 አይሁድ እነዚህን ሁሉ ቀኖች እንደ ጽሕፈቱና እንደ ጊዜው በየዓመቱ ይጠብቁ ዘንድ፥ እነዚህም ቀኖች በየትውልዳቸውና በየወገናቸው በየአገራቸውም በየከተማቸውም የታሰቡና የተከበሩ ይሆኑ ዘንድ፥ እነዚህም የፉሪም ቀኖች በአይሁድ ዘንድ እንዳይሻሩ፥ መታሰባቸውም ከዘራቸው እንዳይቈረጥ፥ በራሳቸውና በዘራቸው ወደ እነርሱም በተጠጉት ሁሉ ላይ እንዳይቀር ሥርዓት አድርገው ተቀበሉ።

参见章节 复制




አስቴር 9:27
18 交叉引用  

በየትኛውም አገርና በማንኛይቱም ከተማ የንጉሡ ዐዋጅ በተነበበበት ስፍራ ሁሉ በአይሁድ ዘንድ ተድላና ደስታ ሆነ፤ በዚሁ ምክንያት አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ከሌሎች አሕዛብ ወገኖች ብዙዎቹ የአይሁድን ሃይማኖት ተቀበሉ።


መርዶክዮስም የዚህን ሁሉ ድርጊት ታሪክ ጽፎ በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ በቅርብም በሩቅም ወደሚኖሩት አይሁድ ሁሉ በደብዳቤ ላከው።


በየዓመቱ የአዳርን ወር ዐሥራ አራተኛና ዐሥራ አምስተኛ ቀን በዓል አድርገው በማክበር እንዲጠብቁት ነገራቸው።


እነዚህ የፑሪም ቀኖች በየትውልዱ፥ በየቤተሰቡ፥ በየሀገሩና በየከተማው መከበር እንዳለባቸው ተወሰነ፤ እነዚህም ቀኞች ሳይከበሩ መቅረት የለባቸውም፤ ከትውልዱም መካከል መታሰቢያነታቸው መቋረጥ የለበትም።


በዚህ ዐይነት እነርሱም በእግዚአብሔር ላይ ይታመናሉ፤ ትእዛዞቹንም ዘወትር ይፈጽማሉ እንጂ ያደረገውን ሁሉ አይረሱም።


ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”


ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ ባዕድ ሰው “እግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ይለየኛል” ብሎ አያስብ፤ ጃንደረባ የሆነ ሰው ልጅ ባለመውለዱ፦ “እንደ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።


ከባዕድ አገር መጥተው፥ ወደ እግዚአብሔር በመጠጋት እርሱን የሚወዱትንና የሚያገለግሉትን፥ የእርሱን ሰንበት ሳይሽሩ በማክበር ቃል ኪዳኑን የሚጠብቁትን ባዕዳንን እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦


ታላቅና ታናሽ እኅቶችሽን ወስጄ ለአንቺ እንደ ልጆችሽ አድርጌ በምሰጥበት ጊዜ የቀድሞውን አካሄድሽን አስታውሰሽ ታፍሪአለሽ። ይህ የሚሆነው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት አይደለም።


በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።


በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”


እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ።


ቃል ኪዳን ያደረገውም ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን፥ አሁን በሕይወት ካለነውም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው።


ስለዚህም ኢያሱ ከእነርሱ ጋር ለሕይወታቸው ዋስትና ቃል ኪዳን በመግባት የሰላም ስምምነት አደረገ። የእስራኤል ሕዝብ መሪዎችም ስምምነቱን ለመጠበቅ ቃል ገቡላቸው።


የእስራኤላውያን ወጣት ሴቶች ልጆች በየዓመቱ ለአራት ቀን ያኽል ከቤታቸው ርቀው እየሄዱ ለገለዓዳዊው ለዮፍታሔ ሴት ልጅ ማዘናቸውና ማልቀሳቸው የተለመደ ሆነ።


ዳዊትም ከዚያን ቀን ጀምሮ ይህን እንደ ሕግና ሥርዓት አድርጎ ስለ ተጠቀመበት በእስራኤል ምድር እስከ ዛሬ ድረስ ሲሠራበት ይኖራል።


跟着我们:

广告


广告