Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ነገር ግን አስቴር ወደ ንጉሡ ቀረበች፤ ንጉሡም ትእዛዙን በጽሑፍ እንዲተላለፍ አደረገ፤ ያም ትእዛዝ ባስገኘው ውጤት ሃማን አይሁድን ለመደምሰስ ዐቅዶት የነበረው ሤራ በራሱ ላይ እንዲመለስበት ሆነ፤ እርሱና ዐሥር ልጆቹ በእንጨት ላይ ተሰቀሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሤራው በንጉሡ ዘንድ እንደ ታወቀ ሐማ በአይሁድ ላይ የሸረበው ሤራ በገዛ ራሱ ላይ እንዲጠመጠም፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹም በዕንጨት ላይ እንዲሰቀሉ የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አስቴርም ወደ ንጉሡ ፊት በገባች ጊዜ በአይሁድ ላይ የተተነኰለው ክፉ ተንኰል በራሱ ላይ እንዲመለስ፥ እርሱና ልጆቹም በግንድ ላይ እንዲሰቀሉ በደብዳቤው አዘዘ።

参见章节 复制




አስቴር 9:25
19 交叉引用  

በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራው ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፥ ንጹሑም ነጻ እንዲወጣ አድርግ።


በተለይም መርዶክዮስ አይሁዳዊ መሆኑን በተረዳ ጊዜ መርዶክዮስን ብቻ መግደል በቂ እንዳልሆነ ተገነዘበ፤ ስለዚህም በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉትን የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድን ሁሉ ለማጥፋት ዕቅድ አወጣ።


ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።


እነሆ እኔና ወገኖቼ ለባርነት መሸጥ አንሶን ለመገደልና ለመደምሰስ ቀርበናል፤ ለባርነት ከመሸጥ የከፋ ነገር ባይደርስብን ኖሮ፥ ዝም ባልኩና እርስዎን ለማስቸገር ባልደፈርኩ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ልንጠፋና ከምድር ገጽ ልንደመሰስ ተፈርዶብናል!” ስትል መለሰችለት።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ “ይህን ለማድረግ የደፈረ ማን ነው? ለመሆኑ ይህ ሰው የት ይገኛል?” ሲል ንግሥት አስቴርን ጠየቃት።


ለክፉዎች የሚፈልጉትን ነገር አትስጣቸው፤ ዕቅዳቸው እንዲሰምር አታድርግ።


የከበቡኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ያቀዱትን ሤራ በእነርሱ ላይ እንዲፈጸም አድርግ።


እኔ ያለ ጒዳት ሳልፍ ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይያዙ።


የሚያመጡት ችግር በራሳቸው ላይ ይደርሳል፤ በክፉ ድርጊታቸውም ዐናታቸው ይፈጠፈጣል።


ስለ እውነተኛነቱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ለልዑል አምላክ ስም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።


እርሱ ስለ ክፋታቸው ይቀጣቸዋል፤ ስለ ኃጢአታቸውም ይደመስሳቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ያጠፋቸዋል።


ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


በዚያም ቀን የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህ ሁሉ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ግን ጠንካራው የዕቃ መስቀያ ኲላብ ተነቅሎ ይወድቃል፤ በኲላቡም ላይ ተሰቅሎ የነበረው ዕቃ ሁሉ ተሰባብሮ ይወድቃል።’ ” ይህን የተናገረ እግዚአብሔር ነው።


“እኔ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ የምፈርድበት ቀን ደርሶአል፤ ኤዶም ሆይ! እንደ ሥራህ ዋጋህን ታገኛለህ፤ የምትፈጽመው ክፉ ሥራ በራስህ ላይ ይመለሳል።


በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰበራል፤ ድንጋዩ በላዩ ላይ የሚወድቅበት ሰው ግን ይጨፈለቃል።”]


ዳዊትም የናባልን መሞት በሰማ ጊዜ “እኔን በመስደቡ እግዚአብሔር ናባልን ስለ ተበቀለውና እኔንም ከስሕተት ስለ ጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ ናባልን ስለ ክፉ ሥራው ቀጥቶታል” አለ። ከዚህም በኋላ ዳዊት ወደ አቢጌል መልእክተኛ ልኮ ሊያገባት መፈለጉን ገለጠላት።


跟着我们:

广告


广告