Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 መርዶክዮስም የዚህን ሁሉ ድርጊት ታሪክ ጽፎ በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ በቅርብም በሩቅም ወደሚኖሩት አይሁድ ሁሉ በደብዳቤ ላከው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 መርዶክዮስ የተፈጸሙትን እነዚህን ድርጊቶች ጻፈ፤ ደብዳቤ አዘጋጅቶም በመላው የንጉሥ ጠረክሲስ አውራጃ በቅርብና በሩቅ ለሚገኙት አይሁድ ሁሉ ላከ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 መርዶክዮስም ይህን ነገር ጻፈ፥ በንጉሡም በአርጤክስስ አገሮች ሁሉ በቅርብና በሩቅ ወዳሉት አይሁድ ሁሉ ደብዳቤዎችን ላከ።

参见章节 复制




አስቴር 9:20
16 交叉引用  

አገልጋዮቹ የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።


ንጉሥ አርጤክስስ ከሕንድ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ያሉትን መቶ ኻያ ሰባት አገሮችን ይገዛ ነበር።


ስለዚህም ንጉሡ “እያንዳንዱ ባል የቤቱ አባወራ ሆኖ በአዛዥነት የመናገር መብቱ የተጠበቀ ይሁን!” የሚል ትእዛዝ በየቋንቋውና በየአጻጻፍ ሥርዓቱ ተዘጋጅቶ ወደያንዳንዱ አገር እንዲተላለፍ አደረገ።


ስለዚህ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ሃማን የንጉሡን ጸሐፊዎች ጠርቶ ዐዋጁ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተተርጒሞ፥ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በሚገኘው የአጻጻፍ ሥርዓት ሁሉ በመዘጋጀት፥ ወደ አገረ ገዢዎችና ወደ ባለሥልጣኖች ሁሉ እንዲላክ ያደርጉ ዘንድ አዘዘ፤ ዐዋጁም በንጉሥ አርጤክስስ ስም ተጽፎ የቀለበቱ ማኅተም ተደርጎበት ተላለፈ።


ይህም የሆነው ሲዋን ተብሎ የሚጠራው ሦስተኛ ወር በገባ በሃያ ሦስተኛው ቀን ነበር፤ መርዶክዮስ የንጉሡን ጸሐፊዎች ሁሉ ጠርቶ ለአይሁድ፥ ከሕንድ እስከ ኢትዮጵያ ያሉትን መቶ ኻያ ሰባት አገሮች ለሚያስተዳድሩ አገረ ገዢዎችና ሌሎችም ባለሥልጣኖች የሚላኩ ደብዳቤዎችን አስጻፈ፤ ደብዳቤዎቹም በእያንዳንዱ አገር ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት እንዲሁም በአይሁድ ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትለው እንዲጻፉ ተደረገ።


በታናናሽ ከተሞች የሚኖሩ አይሁድ አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር ዐሥራ አራተኛውን ዕለት የበዓል ቀን በማድረግ ሲበሉና ሲጠጡ እርስ በርሳቸውም አንዱ ለሌላው የምግብ ስጦታ ሲለዋወጡ የሚውሉት ስለዚህ ነው።


በየዓመቱ የአዳርን ወር ዐሥራ አራተኛና ዐሥራ አምስተኛ ቀን በዓል አድርገው በማክበር እንዲጠብቁት ነገራቸው።


እነዚህ የበዓላት ቀኖች “ፑሪም” ተብለው የሚጠሩትም በዚሁ ምክንያት ነው፤ መርዶክዮስ የላከውን ደብዳቤ መሠረት በማድረግና በዐይናቸው ያዩትንና የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ በማስታውስ፥


አይሁድ ለራሳቸው፥ ለዘሮቻቸው አይሁዳዊ መሆን ለሚፈልግ ሁሉ ቋሚ ደንብ አደረጉ፤ ይኸውም በየዓመቱ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ መርዶክዮስ በሰጠው መመሪያ መሠረት እነዚህ ሁለት ቀኖች ባለማቋረጥ ይከበራሉ።


ከዚህም ሁሉ በኋላ የአቢኀይል ልጅ ንግሥት አስቴር ከመርዶክዮስ ጋር በመተባበር ስለ ፑሪም፥ መርዶክዮስ ቀደም ሲል የላከውን ደብዳቤ በማጠናከር ያላትን ሥልጣን የሚገልጥ ትእዛዝ ያለበት ደብዳቤ ጽፋ ላከች።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።


ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ለወሰዳቸው ካህናትና ነቢያት ለሕዝብ አለቆችና ለሌሎችም ስደተኞች ሁሉ ከኢየሩሳሌም የጻፍኩት ደብዳቤ ይዘት እንዲህ የሚል ነው፤


跟着我们:

广告


广告