Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በታናናሽ ከተሞች የሚኖሩ አይሁድ አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር ዐሥራ አራተኛውን ዕለት የበዓል ቀን በማድረግ ሲበሉና ሲጠጡ እርስ በርሳቸውም አንዱ ለሌላው የምግብ ስጦታ ሲለዋወጡ የሚውሉት ስለዚህ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በየመንደሩ የሚኖሩ የገጠር አይሁድ፣ የአዳርን ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን የተድላና የደስታ፣ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚለዋወጡበት ቀን አድርገው የሚያከብሩት ከዚሁ የተነሣ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ስለዚህም በመንደሮችና ባልተመሸጉ ከተሞች የሚኖሩ አይሁድ አዳር በሚባለው ወር አሥራ አራተኛውን ቀን የደስታና የመጠጥ የመልካምም ቀን፥ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡበት ቀን ያደርጉታል።

参见章节 复制




አስቴር 9:19
13 交叉引用  

በየትኛውም አገርና በማንኛይቱም ከተማ የንጉሡ ዐዋጅ በተነበበበት ስፍራ ሁሉ በአይሁድ ዘንድ ተድላና ደስታ ሆነ፤ በዚሁ ምክንያት አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ከሌሎች አሕዛብ ወገኖች ብዙዎቹ የአይሁድን ሃይማኖት ተቀበሉ።


መርዶክዮስም የዚህን ሁሉ ድርጊት ታሪክ ጽፎ በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ በቅርብም በሩቅም ወደሚኖሩት አይሁድ ሁሉ በደብዳቤ ላከው።


እነዚህም ዕለቶች አይሁድ ራሳቸውን ከጠላቶቻቸው እጅ በማዳን ዕረፍት ያገኙባቸው ቀኖች ናቸው፤ ከሐዘንና ከተስፋ መቊረጥ ወደ ደስታና ወደ ሐሴት የተላለፉት በዚህ ወር ነበር፤ በእነዚህ ዕለቶች በዓል አድርገው በመብላትና በመጠጣት እየተደሰቱ፥ እርስ በርሳቸው አንዳቸው ለሌላው የምግብ ስጦታ እየተለዋወጡና ለድኾችም ስጦታ እየሰጡ እንዲጠብቁአቸው ተነገራቸው።


የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው።


በብርጭቋችሁና በሳሕናችሁ ውስጥ ያለውን ለድኾች ስጡ፤ ከዚህ በኋላ ሁሉ ነገር ንጹሕ ይሆንላችኋል።


“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር በምትኖርባቸው ከተሞች ሁሉ አንድ እስራኤላዊ ችግረኛ ሆኖ ቢገኝ የገዛ ወገንህ ስለ ሆነ አትጨክንበት፤ ገንዘብህንም አትንፈገው።


ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ በከተሞችህ ከሚኖሩት ሌዋውያን፥ በአገርህ የሚኖሩ መጻተኞች፥ እናትና አባት ከሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት እርሱ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን በመረጠው ቦታ በአንድነት ተሰብስበህ ደስ ይበልህ።


እርሱንም ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ፥ በከተሞችህ ከሚኖሩት ሌዋውያን፥ በአገርህ ከሚኖሩ መጻተኞች፥ እናትና አባት ከሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ጋር አብረህ በመሆን ተደሰት።


እነዚህም ሁሉ ከተሞች ከፍ ያለ ቁመት ባላቸው ቅጽሮች የተመሸጉ ነበሩ፤ የቅጽሮቹም በሮች በመወርወሪያ የሚዘጉ ነበሩ፤ ቅጽር የሌላቸው ብዙ መንደሮችም ነበሩ።


እነዚህ ሁለቱ ነቢያት የምድር ሰዎችን አስጨንቀው ስለ ነበረ በምድር የሚኖሩ ሰዎች በነቢያቱ ሞት ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።


እነርሱንም ብትጠይቃቸው ይህንኑ ይነግሩሃል፤ እነሆ ዛሬ እኛ የደስታ ግብዣ በሚደረግበት ቀን መጥተናል፤ እኛንም በመልካም ሁኔታ ትቀበለን ዘንድ ዳዊት ጠይቆአል፤ ስለዚህ ለእኛ ለአገልጋዮችህና ለወዳጅህ ለዳዊት ስትል የሚቻልህን ስጦታ አድርግልን።”


跟着我们:

广告


广告