Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በሱሳ ከተማ የሚኖሩት አይሁድ ግን በዐሥራ ሦስተኛውና በዐሥራ አራተኛው ቀን ሲገድሉ ቈይተው በዐሥራ አምስተኛው ቀን ስላቆሙ በዚሁ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል አድርገው በተድላ ደስታ ዋሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ ግን በዐሥራ ሦስተኛውና በዐሥራ አራተኛው ቀን ተሰብስበው ነበር፤ ከዚያም በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ዐረፉ፤ ዕለቱንም የተድላና የደስታ ቀን አድርገው ዋሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በሱሳ የነበሩት አይሁድ ግን በአሥራ ሦስተኛውና በአሥራ አራተኛው ቀን ተሰበሰቡ፥ በአሥራ አምስተኛውም ቀን ዐረፉ፥ የመጠጥና የደስታም ቀን አደረጉት።

参见章节 复制




አስቴር 9:18
7 交叉引用  

የንጉሡም ዐዋጅ አይሁድ በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ተሰባስበው ራሳቸውን ለመከላከል እንዲደራጁ መብት ይሰጣቸዋል፤ ይኸውም ከየትኛውም ወገንና አገር ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ለማጥቃት የሚነሣውን ማንኛውንም የታጠቀ ኀይል ለማጥፋት፥ ለመግደልና ለመደምሰስ፥ እንዲሁም የጠላቶቻቸውን ሀብትና ንብረት ለመማረክና ለመውሰድ መብት ይሰጣቸዋል።


አዳር ተብሎ የሚጠራው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን እነሆ ደረሰ፤ ያም ዕለት የአይሁድ ጠላቶች ሁሉ አይሁድን በቊጥጥራቸው ሥር ስለ ማድረግ የወጣውን ንጉሣዊ ዐዋጅ ለመፈጸም የተዘጋጁበት ቀን ነበር፤ ነገር ግን ሁኔታው ተለውጦ አይሁድ በእነርሱ ላይ ድልን ተቀዳጁ።


በዚያም ዕለት የተገደሉት ሰዎች ብዛት ምን ያኽል እንደ ሆነ ለንጉሡ ተነገረው።


አስቴርም “የግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ ከሆነስ በሱሳ ከተማ የሚኖሩት አይሁድ ዛሬ ያደረጉትን በነገውም ዕለት ደግመው እንዲያደርጉት ይፈቀድላቸው፤ የዐሥሩም የሃማን ልጆች አስከሬን ተወሰዶ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል እዘዝ” ስትል መለሰችለት።


አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ እንደገና በአንድነት ተደራጅተው በተጨማሪ ሦስት መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ዘረፋ አላካሄዱም።


በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየከተማው አይሁድ በመኖሪያ ሰፈራቸው ሁሉ ጒዳት ሊያደርስባቸው በሚፈልግ በማንኛውም ሰው ላይ አደጋ ለመጣል በሚያስችላቸው ሁኔታ ተደራጁ፤ በየትኛውም ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ስለ ፈሩአቸው ማንም እነርሱን ለመቋቋም አልደፈረም።


በየዓመቱ የአዳርን ወር ዐሥራ አራተኛና ዐሥራ አምስተኛ ቀን በዓል አድርገው በማክበር እንዲጠብቁት ነገራቸው።


跟着我们:

广告


广告