Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እንዲሁም በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየሀገሩ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ አንድነታቸውን በማጠናከር ተደራጅተው ራሳቸውን ተከላከሉ፤ ይጠሉአቸው የነበሩትንም ሰባ አምስት ሺህ ሕዝብ በመግደል ከጠላቶቻቸው እጅ ራሳቸውን አዳኑ፤ ይሁን እንጂ ምንም ዐይነት የንብረት ዝርፊያ አላካሄዱም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚህ ጊዜ በሌሎች በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩ የተቀሩት አይሁድ ራሳቸውን ለመከላከልና ከጠላቶቻቸውም ለመገላገል ተሰበሰቡ፤ ከሚጠሏቸውም ሰባ ዐምስት ሺሕ ገደሉ፤ በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የቀሩትም በንጉሡ አገር ያሉ አይሁድ ተሰብስበው ለሕይወታቸው ቆሙ፥ ከጠላቶቻቸውም ዐረፉ፥ ከሚጠሉአቸውም ሰባ አምስት ሺህ ገደሉ፥ ነገር ግን ወደ ብዝበዛው እጃቸውን አልዘረጉም።

参见章节 复制




አስቴር 9:16
6 交叉引用  

የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች ወደሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ እኅታቸው የተደፈረችበትን ከተማ በሙሉ ዘረፉ።


የንጉሡም ዐዋጅ አይሁድ በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ተሰባስበው ራሳቸውን ለመከላከል እንዲደራጁ መብት ይሰጣቸዋል፤ ይኸውም ከየትኛውም ወገንና አገር ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ለማጥቃት የሚነሣውን ማንኛውንም የታጠቀ ኀይል ለማጥፋት፥ ለመግደልና ለመደምሰስ፥ እንዲሁም የጠላቶቻቸውን ሀብትና ንብረት ለመማረክና ለመውሰድ መብት ይሰጣቸዋል።


በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየከተማው አይሁድ በመኖሪያ ሰፈራቸው ሁሉ ጒዳት ሊያደርስባቸው በሚፈልግ በማንኛውም ሰው ላይ አደጋ ለመጣል በሚያስችላቸው ሁኔታ ተደራጁ፤ በየትኛውም ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ስለ ፈሩአቸው ማንም እነርሱን ለመቋቋም አልደፈረም።


እንደዚህ ቢያደርጉ መንግሥታትን ለማሸነፍ፥ አሕዛብንም ለመቅጣት፥


ነገር ግን ሰይፋቸው የራሳቸውን ልብ ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል።


跟着我们:

广告


广告