Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ እንደገና በአንድነት ተደራጅተው በተጨማሪ ሦስት መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ዘረፋ አላካሄዱም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ አዳር በተባለው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በአንድነት መጡ፤ በሱሳም ሦስት መቶ ሰዎች ገደሉ፤ በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሱሳም የነበሩ አይሁድ አዳር በሚባለው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ደግሞ ተሰብስበው በሱሳ ሦስት መቶ ያህል ሰዎች ገደሉ፥ ነገር ግን ወደ ብዝበዛው እጃቸውን አልዘረጉም።

参见章节 复制




አስቴር 9:15
10 交叉引用  

የንጉሡም ዐዋጅ አይሁድ በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ተሰባስበው ራሳቸውን ለመከላከል እንዲደራጁ መብት ይሰጣቸዋል፤ ይኸውም ከየትኛውም ወገንና አገር ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ለማጥቃት የሚነሣውን ማንኛውንም የታጠቀ ኀይል ለማጥፋት፥ ለመግደልና ለመደምሰስ፥ እንዲሁም የጠላቶቻቸውን ሀብትና ንብረት ለመማረክና ለመውሰድ መብት ይሰጣቸዋል።


ንጉሡም ንግሥት አስቴርን “እነሆ አይሁድ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ብቻ እንኳ የገደሉአቸው ሰዎች ቊጥር ዐሥሩን የሃማንን ወንዶች ልጆች ጨምሮ አምስት መቶ ደርሶአል፤ በየሀገሩ የገደሉአቸውማ ከዚህ እጅግ ሳይበልጥ አይቀርም፤ ታዲያ፥ አሁን ከዚህ ሌላ ምን ትፈልጊያለሽ? ይፈጸምልሻል፤ የምትፈልጊውን ንገሪኝ ይሰጥሻል!” አላት።


አስቴርም “የግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ ከሆነስ በሱሳ ከተማ የሚኖሩት አይሁድ ዛሬ ያደረጉትን በነገውም ዕለት ደግመው እንዲያደርጉት ይፈቀድላቸው፤ የዐሥሩም የሃማን ልጆች አስከሬን ተወሰዶ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል እዘዝ” ስትል መለሰችለት።


ይህም እንዲፈጸም ንጉሡ ትእዛዝ ሰጠ፤ በሱሳ ከተማም እንደገና ዐዋጅ ተነገረ፤ የሃማን ዐሥር ልጆች አስከሬንም በይፋ ለሕዝብ እንዲታይ ተደርጎ ተሰቀለ።


እንዲሁም በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየሀገሩ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ አንድነታቸውን በማጠናከር ተደራጅተው ራሳቸውን ተከላከሉ፤ ይጠሉአቸው የነበሩትንም ሰባ አምስት ሺህ ሕዝብ በመግደል ከጠላቶቻቸው እጅ ራሳቸውን አዳኑ፤ ይሁን እንጂ ምንም ዐይነት የንብረት ዝርፊያ አላካሄዱም።


በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየከተማው አይሁድ በመኖሪያ ሰፈራቸው ሁሉ ጒዳት ሊያደርስባቸው በሚፈልግ በማንኛውም ሰው ላይ አደጋ ለመጣል በሚያስችላቸው ሁኔታ ተደራጁ፤ በየትኛውም ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ስለ ፈሩአቸው ማንም እነርሱን ለመቋቋም አልደፈረም።


ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።


ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል።


跟着我们:

广告


广告