Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 8:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይሁን እንጂ የቤተ መንግሥቱ ማኅተም ያለበትና በንጉሡ ስም የተላለፈ ዐዋጅ ሊለወጥ አይችልም፤ ሆኖም እናንተ በበኩላችሁ የፈለጋችሁትን ነገር ለአይሁድ ጻፉላቸው፤ በእኔም ስም ከጻፋችሁ በኋላ የቤተ መንግሥቱን ማኅተም አትሙበት።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በንጉሥ ስም የተጻፈና በቀለበቱ የታተመ ደብዳቤ ሊሻር ስለማይችል፣ እናንተ ደግሞ አይሁድን በተመለከተ መልካም መስሎ የታያችሁን ሌላ ዐዋጅ በንጉሡ ስም ጽፋችሁ በንጉሡ የቀለበት ማኅተም ዐትሙት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በንጉሡ ስም የተጻፈና በንጉሡ ቀለበት የታተመ አይገለበጥምና እናንተ ደግሞ ደስ የሚያሰኛችሁን በንጉሡ ስም ስለ አይሁድ ጻፉ፥ በንጉሡም ቀለበት አትሙ አላቸው።

参见章节 复制




አስቴር 8:8
9 交叉引用  

ከዚህም በኋላ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋ በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱኑ ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች።


ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ መልካም ፈቃድህ ቢሆን፥ ንግሥት አስጢን ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ ፊት መቅረብ ከቶ እንዳይፈቀድላት የሚገልጥ ውሳኔህን በዐዋጅ አስተላልፍ፤ ይህም ውሳኔ ከቶ የማይለወጥ ሆኖ ለዘለዓለም ይጸና ዘንድ በፋርስና በሜዶን ሕግ ውስጥ እንዲመዘገብ ትእዛዝ አስተላልፍ፤ የአስጢንንም የንግሥትነት ማዕርግ ከእርስዋ ለተሻለች ለሌላ ሴት ስጥ።


ስለዚህ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ሃማን የንጉሡን ጸሐፊዎች ጠርቶ ዐዋጁ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተተርጒሞ፥ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በሚገኘው የአጻጻፍ ሥርዓት ሁሉ በመዘጋጀት፥ ወደ አገረ ገዢዎችና ወደ ባለሥልጣኖች ሁሉ እንዲላክ ያደርጉ ዘንድ አዘዘ፤ ዐዋጁም በንጉሥ አርጤክስስ ስም ተጽፎ የቀለበቱ ማኅተም ተደርጎበት ተላለፈ።


መርዶክዮስ ደብዳቤዎቹን ሁሉ በንጉሥ አርጤክስስ ስም አስጽፎ የቤተ መንግሥቱን ማኅተም አተመባቸው፤ ደብዳቤዎቹም በቤተ መንግሥቱ ጋጥ በተቀለቡ ፈጣን ፈረሶች በሚጋልቡ ጋላቢዎች እጅ እንዲላኩ አደረገ።


“የግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ ቢሆንና ስለ እኔም የሚያስብልኝ ከሆነ፥ እንዲሁም ጉዳዩ በእርስዎ ፊት ትክክል ሆኖ ከተገኘ፥ በንጉሠ ነገሥት ግዛትዎ ሁሉ ውስጥ የሚገኙ አይሁድ ሁሉ ይደመሰሱ ዘንድ የአጋግ ዘር የነበረው የሃመዳታ ልጅ ሃማን ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ የሚሽር ዐዋጅ እንዲያስተላልፉልኝ እለምንሃለሁ።


እንግዲህ ንጉሥ ሆይ! ይህ ዐዋጅ እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ የጠበቀና የማይለወጥ እንዲሆን ፈርምበት።”


ነገር ግን “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ጸንቶ ይኖራል።


跟着我们:

广告


广告