16 ይህም ሁኔታ ለአይሁድ ተድላና ደስታ፥ ሐሴትና ክብር ነበር።
16 ጊዜውም ለአይሁድ የደስታና የፈንጠዝያ፣ የተድላና የክብር ወቅት ሆነላቸው።
16 ለአይሁድም ብርሃንና ደስታ ተድላና ክብርም ሆነ።
“ሄደህ በሱሳ የሚገኙትን አይሁድ በአንድነት ሰብስብ፤ ጾም ዐውጃችሁም ለእኔ ጸልዩ፤ እስከ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም ዐይነት ምግብ አትብሉ፤ ምንም ዐይነት መጠጥ አትጠጡ፤ እኔና ደንገጡሮቼም በዚሁ ዐይነት እንቈያለን፤ ከዚህም በኋላ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ደፍሬ ወደ ንጉሡ ዘንድ እገባለሁ፤ ይህን በማድረጌ ብሞትም ልሙት።”
ይህም የሆነው አዳር የተባለው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ነበር፤ በተከታዩ ዐሥራ አራተኛ ቀን ግን ምንም ግድያ ሳያካሄዱ የተድላ ደስታ ቀን አድርገውት ዋሉ።
ምሕረትና ቸርነት፥ ቅንነትም ለሚያደርግ ለደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃንን ሰጥቶናል፤ ለምለም የሆኑ ቅርንጫፎችን ይዘን በዓል ለማክበር ወደ መሠዊያው እንሂድ።
እግዚአብሔር ሆይ! ለእኔ ብርሃኔ ነህ፤ አንተ አምላኬ ጨለማዬን ታበራለህ።
ስለዚህ ዝም አልልም፤ ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ስለዚህ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
ብርሃን ለደጋግ ሰዎች፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ይወጣላቸዋል።
ለጻድቃን፥ ሁሉ ነገር ሲሳካላቸው በከተማው ውስጥ ደስታ ይሆናል። ክፉዎች ሲጠፉ ደግሞ እልልታ ይሆናል።
ደጋግ ሰዎች ድል በሚያደርጉበት ጊዜ ሰው ሁሉ ይደሰታል፤ ክፉ ሰዎች ሥልጣን በሚይዙበት ጊዜ ግን ሰው ሁሉ በሐዘን አንገቱን ይደፋል።
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።