Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መርዶክዮስ ሰማያዊና ነጭ የቤተ መንግሥት ልብስ ለብሶ፣ ትልቅ የወርቅ አክሊል ደፍቶ፣ ከቀጭን በፍታና ከሐምራዊ ግምጃ የተሠራ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ ከንጉሡ ፊት ወጣ፤ የሱሳ ከተማም ደስታ የተሞላበት በዓል አከበረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 መርዶክዮስም በሰማያዊና በነጭ ሐር የተሠራውን የንጉሡን የክብር ልብስ ለብሶ ታላቅም የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከጥሩ በፍታና ከሐምራዊ ግምጃ የተሠራ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ ከንጉሡ ፊት ወጣ፥ የሱሳም ከተማ ደስ አላት፥ እልልም አለች።

参见章节 复制




አስቴር 8:15
15 交叉引用  

ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።


የአትክልት ቦታውም ከነጭ ጥጥ በፍታ በተሠሩ ሰማያዊ ቀለም ባላቸው መጋረጃዎች የተጌጠ ነበር፤ መጋረጃዎቹም ከሐምራዊ በፍታ በተሠሩና የብር ቀለበት በተበጀላቸው ገመዶች በዕብነ በረድ ምሰሶዎች ላይ ተንጠልጥለው ነበር፤ ከወርቅና ከብር የተሠሩ ድንክ አልጋዎችም ነጭና ቀይ፥ ቢጫና ሰማያዊ ቀለማትን በሚፈነጥቅ የዕብነ በረድ ወለል ላይ ተደርድረው ነበረ።


እርሱ ያደረጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ መርዶክዮስንም ከፍ ከፍ በማድረግ እንዴት ወደ ታላቅ ማዕርግና ልዕልና እንዳደረሰው የሚገልጠው ታሪክ በፋርስና በሜዶን ነገሥታት የታሪክ መዝገብ ላይ በጽሑፍ እንዲሰፍር ተደርጓል።


በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።


ጾም በጀመረች በሦስተኛውም ቀን አስቴር ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳ በዙፋኑ ክፍል ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው የቤተ መንግሥት አደባባይ ገብታ ቆመች፤ ንጉሡም በዚያው ክፍል ውስጥ ከመግቢያው በር ፊት ለፊት በተዘረጋ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር።


ምን ያኽል ሀብታም እንደ ሆነና ምን ያኽል ልጆች እንዳሉት፥ ንጉሡም ሥልጣኑን ከፍ በማድረግና በመሾም የቱን ያኽል እንዳከበረው፥ ከሌሎቹ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይበልጥ የተከበረ ሰው መሆኑንም በትምክሕት ገለጠላቸው፤


ስለዚህም ሃማን ልብሰ መንግሥትና ፈረስ አዘጋጅቶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ መርዶክዮስ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠም በኋላ ሃማን ፊት ፊት እየሄደ በመምራት “ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!” እያለ ያውጅ ነበር።


ፈረሰኞቹም በንጉሡ ትእዛዝ በቤተ መንግሥት ፈረሶች ላይ ተቀምጠው በፍጥነት ጋለቡ፤ ይኸው ንጉሣዊ ትእዛዝ የመናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳም በይፋ ለሕዝብ እንዲነገር ተደረገ።


ለጻድቃን፥ ሁሉ ነገር ሲሳካላቸው በከተማው ውስጥ ደስታ ይሆናል። ክፉዎች ሲጠፉ ደግሞ እልልታ ይሆናል።


ደጋግ ሰዎች ድል በሚያደርጉበት ጊዜ ሰው ሁሉ ይደሰታል፤ ክፉ ሰዎች ሥልጣን በሚይዙበት ጊዜ ግን ሰው ሁሉ በሐዘን አንገቱን ይደፋል።


ደጋግ ሰዎች ሲሾሙ ሕዝቦች ይደሰታሉ፤ ክፉ ሰዎች ሲሾሙ ግን ሕዝቦች ይጨነቃሉ።


ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ።


ነገር ግን ሰሎሞንስ እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ፥ ከእነርሱ እንደ አንዲቱ አለበሰም እላችኋለሁ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር።


跟着我们:

广告


广告