አስቴር 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከልዑላን መሳፍንቱ አንዱን አስጠርተህ ልብሰ መንግሥቱን ይስጠውና በተዘጋጀለት ፈረስ ላይ አስቀምጦ ፊት ለፊት እየመራ ወደ ከተማይቱ አደባባይ እንዲያወጣው አድርግ፤ ሁለቱም በሚጓዙበት ጊዜ መስፍኑ ‘ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!’ እያለ ዐዋጅ ይናገር።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚያም ልብሱና ፈረሱ እጅግ ከከበሩት ከንጉሡ ልዑላን መሳፍንት በአንዱ እጅ ይሰጥለት። ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፤ በፈረሱም ላይ አስቀምጠውም በከተማዪቱ ዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመሩ፣ ‘ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ይህ ተደርጎለታል’ ይበሉ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ልብሱንና ፈረሱንም ከንጉሡ አዛውንት በዋነኛው እጅ ያስረክቡት፥ ንጉሡም ያከብረው ዘንድ የሚወድደውን ሰው ያልብሱት፥ በፈረሱም ላይ አስቀምጠውት በከተማይቱ አደባባይ ያሳልፉት፥ በፊቱም፦ ንጉሡ ያከብረው ዘንድ ለሚወድደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል ተብሎ አዋጅ ይነገር። 参见章节 |