Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሃማንም ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ ንጉሡ “ታላቅ ክብር ልሰጠው የፈለግኹት አንድ ሰው አለ፤ ታዲያ ለዚህ ሰው ምን ላደርግለት የሚገባ ይመስልሃል?” ሲል ጠየቀው። ሃማንም “ንጉሡ ይህን ክብር ከእኔ ሌላ ለማን ይሰጣል?” ብሎ በልቡ አሰበ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሐማ በገባ ጊዜ ንጉሡ፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለወደደው ሰው ምን ሊደረግለት ይገባል?” ሲል ጠየቀው። በዚህ ጊዜ ሐማ፣ “ንጉሡ ከእኔ ይልቅ የሚያከብረው ማን አለ?” ሲል በልቡ ዐሰበ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሐማም ገባ፥ ንጉሡም፦ ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ምን ይደረግለታል? አለው። ሐማም በልቡ፦ ንጉሡ ከእኔ ይልቅ ማንን ያከብር ዘንድ ይወድዳል? አለ።

参见章节 复制




አስቴር 6:6
19 交叉引用  

ንጉሡም እነዚህን አማካሪዎች “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስጢንን ያመጡ ዘንድ በማዘዝ አገልጋዮቼን ብልክባት እርስዋ እምቢ ብላ ቀርታለች! ታዲያ፥ በእርስዋ ላይ መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ሕጉ ምን ይላል?” ሲል ጠየቃቸው።


ምን ያኽል ሀብታም እንደ ሆነና ምን ያኽል ልጆች እንዳሉት፥ ንጉሡም ሥልጣኑን ከፍ በማድረግና በመሾም የቱን ያኽል እንዳከበረው፥ ከሌሎቹ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይበልጥ የተከበረ ሰው መሆኑንም በትምክሕት ገለጠላቸው፤


ስለዚህም ሃማን ልብሰ መንግሥትና ፈረስ አዘጋጅቶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ መርዶክዮስ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠም በኋላ ሃማን ፊት ፊት እየሄደ በመምራት “ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!” እያለ ያውጅ ነበር።


ስለዚህም አገልጋዮቹ “እነሆ ሃማን አንተን ለማነጋገር እየጠየቀ ነው” አሉት። ንጉሡም “ግባ በሉት” አለ።


ስለዚህም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ለእንደዚህ ያለው ሰው አንተ ራስህ የለበስከውን ልብሰ መንግሥት እንዲያመጡለት አድርግ፤ አንተም በተቀመጥክበት ፈረስ ራስ ላይ የንጉሣዊ ዘውድ ምልክት እንዲያደርጉበት እዘዝ፤


ከልዑላን መሳፍንቱ አንዱን አስጠርተህ ልብሰ መንግሥቱን ይስጠውና በተዘጋጀለት ፈረስ ላይ አስቀምጦ ፊት ለፊት እየመራ ወደ ከተማይቱ አደባባይ እንዲያወጣው አድርግ፤ ሁለቱም በሚጓዙበት ጊዜ መስፍኑ ‘ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!’ እያለ ዐዋጅ ይናገር።”


ድል ማድረጌ የሚያስደስታቸው ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው! ለአገልጋዩ ሁኔታዎች ሁሉ ሲሳኩለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል!” ይበሉ።


ዕውቀት የጐደላቸው ሰዎች ከጥበብ በመራቃቸው ምክንያት ይሞታሉ፤ ሞኞችም ከቸልተኛነታቸው የተነሣ ይጠፋሉ።


ትዕቢት ወደ ጥፋት ይወስዳል፤ ትምክሕተኛነትም ወደ ውድቀት ያደርሳል።


ትዕቢት ጥፋትን ያመጣል፤ ትሕትና ግን ክብርን ያጐናጽፋል። ክብርን ግን ትሕትና ይቀድመዋል።


በትዕቢት የተሞሉና ሰውን የሚንቁ ሰዎች አሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።


እኔም ለእነርሱ መልካም ነገር በማድረግ ደስ ይለኛል፤ እኔ በፈቃዴ በዚህች ምድር በእውነት እመሠርታቸዋለሁ።


የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤ በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤ የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤ ‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ።


በዚያኑ ጊዜ “እነሆ፥ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።


ታዲያ፥ ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘ይህን ስፍራ ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል፤ ያን ጊዜ በታላቅ ኀፍረት ወደ ዝቅተኛው ቦታ ወርደህ ትቀመጣለህ።


ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።


跟着我们:

广告


广告