አስቴር 6:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ለሚስቱና ለወዳጆቹም የደረሰበትን አሳፋሪ ነገር በሙሉ ነገራቸው፤ ሚስቱና እነዚያ አስተዋዮች የሆኑ ወዳጆቹም “እነሆ በገዛ እጅህ ሥልጣንህን ለመርዶክዮስ ልታስረክብ ተቃርበሃል፤ እርሱ አይሁዳዊ ስለ ሆነ ልትቋቋመው አትችልም፤ በእርግጥም እርሱ ያሸንፍሃል!” አሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ሐማም የደረሰበትን ሁሉ ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ነገራቸው። አማካሪዎቹና ሚስቱ ዞሳራም፣ “በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ዘሩ ከአይሁድ ወገን ከሆነ፣ ልትቋቋመው አትችልም፤ ያለ ጥርጥር ትጠፋለህ” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ሐማም ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ አጫወታቸው። ጥበበኞቹና ሚስቱ ዞሳራም፦ በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ከአይሁድ ወገን የሆነ እንደ ሆነ በፊቱ ፈጽሞ ትወድቃለህ እንጂ አታሸንፈውም አሉት። 参见章节 |