Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንጉሡም ሃማንን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “በል እንግዲህ ፍጠን፤ ልብሰ መንግሥቱንና ፈረሱን አዘጋጅተህ ይህን አሁን ያልከውን ክብር ሁሉ አይሁዳዊ ለሆነው ለመርዶክዮስ አድርግለት፤ እርሱንም አሁን በቤተ መንግሥቱ መግቢያ በር አጠገብ ስለምታገኘው ካሳሰብከው ነገር አንድም ሳይቀር ሁሉንም አድርግለት።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ንጉሡም ሐማን፣ “በል ፈጥነህ ሂድ፤ ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡ በር ላይ ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስም ልክ እንዳልኸው አድርግለት፤ ከተናገርኸውም አንዳች ነገር እንዳይጐድል” ሲል አዘዘው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ንጉሡም ሐማን፦ ፍጠን፥ እንደ ተናገርኸውም ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፥ በንጉሡም በር ለሚቀመጠው አይሁዳዊ ለመርዶክዮስ እንዲሁ አድርግለት፥ ከተናገርኸውም ሁሉ ምንም አይቅር አለው።

参见章节 复制




አስቴር 6:10
7 交叉引用  

ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈጽሞታል።”


ስለዚህም ሃማን ልብሰ መንግሥትና ፈረስ አዘጋጅቶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ መርዶክዮስ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠም በኋላ ሃማን ፊት ፊት እየሄደ በመምራት “ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!” እያለ ያውጅ ነበር።


ከልዑላን መሳፍንቱ አንዱን አስጠርተህ ልብሰ መንግሥቱን ይስጠውና በተዘጋጀለት ፈረስ ላይ አስቀምጦ ፊት ለፊት እየመራ ወደ ከተማይቱ አደባባይ እንዲያወጣው አድርግ፤ ሁለቱም በሚጓዙበት ጊዜ መስፍኑ ‘ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!’ እያለ ዐዋጅ ይናገር።”


እናንተ በእግዚአብሔር ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ ጠንክሩ፤ በርቱም።


“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።”


እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።


跟着我们:

广告


广告