Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያች ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ መተኛት አልቻለም። ስለዚህ በዘመነ መንግሥቱ የተመዘገበው የታሪክ መጽሐፍ ቀርቦ እንዲነበብለት አዘዘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያም ሌሊት እንቅልፍ ከንጉሡ ሸሸ፥ የዘመኑንም ታሪክ መጽሐፍ ያመጡ ዘንድ አዘዘ፥ በንጉሡም ፊት ተነበበ።

参见章节 复制




አስቴር 6:1
12 交叉引用  

አብርሃም ያንን ቦታ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ።


እርሱ ያደረጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ መርዶክዮስንም ከፍ ከፍ በማድረግ እንዴት ወደ ታላቅ ማዕርግና ልዕልና እንዳደረሰው የሚገልጠው ታሪክ በፋርስና በሜዶን ነገሥታት የታሪክ መዝገብ ላይ በጽሑፍ እንዲሰፍር ተደርጓል።


መርዶክዮስ በቤተ መንግሥቱ በር ተቀምጦ በነበረበት ጊዜ ወደ ንጉሡ መኖሪያ ክፍሎች የሚያስገቡትን በሮች ይጠብቁ የነበሩት ቢግታንና ቴሬሽ ተብለው የሚጠሩት ሁለቱ የቤተ መንግሥት ጃንደረቦች በንጉሥ አርጤክስስ ላይ በጠላትነት ተነሣሥተው ሊገድሉት ዐድመው ነበር።


መርዶክዮስ ይህን ዐድማ በሰማ ጊዜ ለንግሥት አስቴር ነገራት፤ አስቴርም በመርዶክዮስ ስም ምሥጢሩን ለንጉሡ ነገረች።


ምርመራም በተደረገ ጊዜ የቀረበው መረጃ እውነት ሆኖ ተገኘ፤ ስለዚህም ሁለቱ ዐመፀኞች በስቅላት ሞት ተቀጡ፤ ንጉሡም ይህ ሁኔታ በንጉሠ ነገሥቱ የታሪክ መዝገብ ተጽፎ እንዲቀመጥ ትእዛዝ አስተላለፈ።


“ድኾችና ችግረኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ አያገኙም፤ ጒሮሮአቸው ከጥማት የተነሣ ሲደርቅ፥ እኔ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን እሰማለሁ፤ እኔም የእስራኤል አምላክ ከቶ አልተዋቸውም።


ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አየ፤ በጣምም ስለ ተጨነቀ እንቅልፍ አጣ።


ንጉሡም ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ ምግብ አልበላም፤ የሚያስደስት ነገርም እንዲቀርብለት ሳይፈልግ እንቅልፍ አጥቶ ዐደረ።


ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም በጥሞና አዳመጣቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ስሙንም የሚያከብሩ ሰዎች ለተግባራቸው መታሰቢያ በመጽሐፍ ተጻፈ።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ ዕውቀትም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ የማይመረመር፥ መንገዱም የማይታወቅ ነው።


跟着我们:

广告


广告