Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የወይን ጠጅ በመጠጣት ላይ ሳሉም ንጉሡ አስቴርን “ማናቸውንም የምትፈልጊውን ነገር ጠይቂኝ፤ ይፈጸምልሻል፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ልሰጥሽ ዝግጁ ነኝ!” አላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ ንጉሡ ዳግመኛ አስቴርን፣ “እስኪ የምትፈልጊው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ ደግሞስ የምትጠይቂው ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይፈቀድልሻል” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ንጉሡም በወይኑ ጠጅ ግብዣ ሳለ አስቴርን፦ የምትሺው ምንድር ነው? ይሰጥሻል፥ ልመናሽስ ምንድር ነው? እስከ መንግሥቴ እኵሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል አላት።

参见章节 复制




አስቴር 5:6
6 交叉引用  

ንጉሠ ነገሥቱም “ታዲያ፥ አሁን የምትፈልገው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ፤ እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ከጸለይሁ በኋላ፥


ንጉሡም “አስቴር ሆይ፥ ስለምን መጣሽ? ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የንጉሠ ነገሥት መንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” አላት።


አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ “በግርማዊነትዎ ፊት ሞገስ አግኝቼ ግርማዊነትዎ የጠየቅሁትን ነገር ሊፈጽምልኝ ፈቃደኛ ከሆነ ነገ በማዘጋጀው ግብዣ ላይ እርስዎና ሃማን በድጋሚ እንድትገኙልኝ በአክብሮት እለምናለሁ፤ በዚያም ሰዓት የምፈልገውን ነገር እገልጥልዎታለሁ።”


የወይን ጠጅ በመጠጣትም ላይ ሳሉ ንጉሡ “አስቴር ሆይ! ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የፈለግሺውን ነገር ሁሉ እፈጽምልሻለሁ፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” ሲል እንደገና ጠየቃት።


ንጉሡም ንግሥት አስቴርን “እነሆ አይሁድ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ብቻ እንኳ የገደሉአቸው ሰዎች ቊጥር ዐሥሩን የሃማንን ወንዶች ልጆች ጨምሮ አምስት መቶ ደርሶአል፤ በየሀገሩ የገደሉአቸውማ ከዚህ እጅግ ሳይበልጥ አይቀርም፤ ታዲያ፥ አሁን ከዚህ ሌላ ምን ትፈልጊያለሽ? ይፈጸምልሻል፤ የምትፈልጊውን ንገሪኝ ይሰጥሻል!” አላት።


“የመንግሥቴንም እኩሌታ እንኳ ቢሆን፥ የምትጠይቂኝን ሁሉ እሰጥሻለሁ!” ሲል ማለላት።


跟着我们:

广告


广告