Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ምን ያኽል ሀብታም እንደ ሆነና ምን ያኽል ልጆች እንዳሉት፥ ንጉሡም ሥልጣኑን ከፍ በማድረግና በመሾም የቱን ያኽል እንዳከበረው፥ ከሌሎቹ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይበልጥ የተከበረ ሰው መሆኑንም በትምክሕት ገለጠላቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሐማ ስለ ሀብቱ ታላቅነት፣ ስለ ልጆቹ ብዛት እንዲሁም ንጉሡ የቱን ያህል እንዳከበረው፣ ከሌሎቹም መኳንንትና ሹማምት ይበልጥ እንዴት ከፍ ከፍ እንዳደረገው እያጋነነ ነገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሐማም የሀብቱን ክብርና የልጆቹን ብዛት፥ ንጉሡም ያከበረበትን ክብር ሁሉ፥ በንጉሡም አዛውንትና ባሪያዎች ላይ ከፍ ከፍ እንዳደረገው አጫወታቸው።

参见章节 复制




አስቴር 5:11
19 交叉引用  

የላባ ወንዶች ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት ወሰደ፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያገኘው ከአባታችን ነው” እያሉ መናገራቸውን ያዕቆብ ሰማ።


ንጉሡም ለስድስት ወራት ያኽል የመንግሥቱን የሀብት ብዛትና የንጉሣዊውን ግርማ ሞገስና ክብር በይፋ እንዲታይ አደረገ።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ የሃመዳታ ልጅ የሆነውን አጋጋዊውን ሐማንን ከሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በላይ ክብሩን በማስበለጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው።


መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።


እንዲሁም በሀብታቸው ብዛት የሚተማመኑና በብልጽግናቸው ብዛት የሚመኩ ክፉ ሰዎች ቢከቡኝስ ለምን እፈራለሁ?


ሰው ራሱን መቤዠትም ሆነ ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም።


አምላክ ሆይ! ስላደረግኸው መልካም ነገር ሁሉ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፤ በአማኞች ፊት ቆሜ ስለ አንተ ቸርነት እናገራለሁ።


ስለዚህም ንጉሣቸው እንዲህ እያለ ይደነፋል፥ “የጦር አዛዦቼ ሁሉ ነገሥታት አይደሉምን?


ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”


ደቀ መዛሙርቱም በቃሉ ተደነቁ፤ ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ልጆች ሆይ! ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው!


የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።


跟着我们:

广告


广告