Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህም በኋላ አስቴር ከቤተ መንግሥቱ ጃንደረቦች መካከል በተለይ እርስዋን እንዲያገለግል ንጉሡ የመደበላትን ሀታክ የተባለውን ጠርታ ወደ መርዶክዮስ ዘንድ ሄዶ ምን እንደ ደረሰበት እንዲጠይቀው ላከችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም አስቴር ከንጉሡ ጃንደረቦች መካከል እርሷን እንዲያገለግል የተመደበውን ሀታክን ጠርታ፣ መርዶክዮስ ምን ችግር እንደ ገጠመውና ስለ ምንስ እንደዚህ እንደ ሆነ እንዲያጣራ ላከችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አስቴርም ያገለግላት ዘንድ ንጉሡ ያቆመውን አክራትዮስን ጠራች እርሱም ከጃንደረቦች አንዱ ነበረ፥ እርስዋም ይህ ነገር ምንና ምን እንደ ሆነ ያስታውቃት ዘንድ ወደ መርዶክዮስ እንዲሄድ አዘዘችው።

参见章节 复制




አስቴር 4:5
10 交叉引用  

ግብዣው በተጀመረ በሰባተኛው ቀን ንጉሥ አርጤክስስ በወይን ጠጅ ረክቶ ደስ ባለው ጊዜ መሁማን፥ ቢዝታ፥ ሐርቦና፥ ቢግታ፥ አባግታ፥ ዜታርና ካርካስ ተብለው የሚጠሩትን ጃንደረቦች የሆኑትን ሰባቱን የእልፍኝ አገልጋዮቹን ወደ እርሱ ጠርቶ፥


ነገር ግን ይህን የንጉሡን ትእዛዝ ለንግሥት አስጢን በነገሩአት ጊዜ ወደ ንጉሡ ፊት ለመቅረብ እምቢ አለች፤ ይህም ሁኔታ ንጉሡን እጅግ አስቈጣው።


አስቴርም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለመርዶክዮስ እንዲነግር ሀታክን መልሳ ላከችው፤


የአስቴር ደንገጡሮችና እርስዋን የሚጠብቁ ጃንደረቦች መርዶክዮስ የሚያደርገውን ሁሉ በነገሩአት ጊዜ ጥልቅ ሐዘን ተሰማት፤ ለመርዶክዮስም በማቅ ፈንታ የሚለብሰውን ልብስ ላከችለት፤ እርሱ ግን አልቀበልም አለ።


ሀታክም ወደ ቤተ መንግሥቱ በሚያስገባው በር አጠገብ በሚገኘው የከተማይቱ አደባባይ ወደሚገኘው ወደ መርዶክዮስ ሄደ።


ሀታክም ይህን ሁሉ ፈጸመ፤


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።


አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንዱ የሰውነት ክፍል ሲከበር ሌሎቹም የሰውነት ክፍሎች አብረው ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ።


እንዲሁም እያንዳንዱ የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም ያስብ።


እኛ ያለን የካህናት አለቃ በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።


跟着我们:

广告


广告