Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ይህን ዐዋጅ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ወደሚገኙት አገሮች ሁሉ እንዲያደርሱ ተላኩ፤ በዐዋጁም ውስጥ አዳር ተብሎ በሚጠራው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን መላውን የአይሁድ ወጣት፥ ሽማግሌ፥ ሴት፥ ወንድ ሳይቀር ሕፃናትንም ጭምር እንዲገድሉ፥ እንዲያጠፉና እንዲደመሰሱ የሚያዝ ቃል ነበረበት፤ ንብረታቸውም ሁሉ እንዲዘረፍ ትእዛዝ ወጥቶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ሕፃን ሳይባል አይሁድ ሁሉ በዚያ ዕለት እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉና እንዲደመሰሱ፣ ሀብታቸውም እንዲዘረፍ ደብዳቤ ለንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ በመልእክተኞች እጅ ተላከ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በአሥራ ሁለተኛው ወር በአዳር በአሥራ ሦስተኛው ቀን አይሁድን ሁሉ፥ ልጆችንና ሽማግሌዎችን፥ ሕፃናቶችንና ሴቶችን፥ በአንድ ቀን ያጠፉና ይገድሉ ዘንድ፥ ይደመስሱም ዘንድ፥ ምርኮአቸውንም ይዘርፉ ዘንድ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች እጅ ወደ ንጉሡ አገሮች ሁሉ ተላኩ።

参见章节 复制




አስቴር 3:13
14 交叉引用  

በንጉሡ ትእዛዝ መልእክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የሕዝቡን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ። “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከአሦር ንጉሥ ምርኮ የተረፋችሁት ወደ እናንተ ይመለስ ዘንድ፥ ወደ አብርሃም፥ ወደ ይስሐቅና ወደ ያዕቆብ አምላክ ተመለሱ፤


እነሆ እኔና ወገኖቼ ለባርነት መሸጥ አንሶን ለመገደልና ለመደምሰስ ቀርበናል፤ ለባርነት ከመሸጥ የከፋ ነገር ባይደርስብን ኖሮ፥ ዝም ባልኩና እርስዎን ለማስቸገር ባልደፈርኩ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ልንጠፋና ከምድር ገጽ ልንደመሰስ ተፈርዶብናል!” ስትል መለሰችለት።


“የግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ ቢሆንና ስለ እኔም የሚያስብልኝ ከሆነ፥ እንዲሁም ጉዳዩ በእርስዎ ፊት ትክክል ሆኖ ከተገኘ፥ በንጉሠ ነገሥት ግዛትዎ ሁሉ ውስጥ የሚገኙ አይሁድ ሁሉ ይደመሰሱ ዘንድ የአጋግ ዘር የነበረው የሃመዳታ ልጅ ሃማን ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ የሚሽር ዐዋጅ እንዲያስተላልፉልኝ እለምንሃለሁ።


አዳር ተብሎ የሚጠራው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን እነሆ ደረሰ፤ ያም ዕለት የአይሁድ ጠላቶች ሁሉ አይሁድን በቊጥጥራቸው ሥር ስለ ማድረግ የወጣውን ንጉሣዊ ዐዋጅ ለመፈጸም የተዘጋጁበት ቀን ነበር፤ ነገር ግን ሁኔታው ተለውጦ አይሁድ በእነርሱ ላይ ድልን ተቀዳጁ።


በዚህ ዐይነት አይሁድ በጠላቶቻቸው ላይ የፈለጉትን ለማድረግ ቻሉ፤ በሰይፍ እያጠቁም ጨፈጨፉአቸው።


“የዕድሜዬ ቀኖች ከሯጭ ይልቅ የፈጠኑ ናቸው ምንም ደስታ ሳላይ ያልፋሉ።


ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”


የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።


እግራቸው ሰውን ለመግደል የፈጠነ ነው፤


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”


ከዚህም በኋላ ሳኦል የካህናት ከተማ በሆነችው በኖብ የሚኖሩት ሁሉ ወንዶችና ሴቶች፥ ልጆችና ሕፃናት፥ የቀንድ ከብቶችና አህዮች፥ እንዲሁም የበግ መንጋዎች ሁሉ እንዲገደሉ አደረገ።


跟着我们:

广告


广告