Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንጉሡም ዐዋጆችን ሁሉ ይፋ የሚያደርግበትን የቀለበት ማኅተም ወስዶ ለአጋጋዊው ለሃመዳታ ልጅ የአይሁድ ጠላት ለሆነው ለሃማን ሰጠው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ስለዚህ ንጉሡ የቀለበት ማኅተሙን ከጣቱ አውልቆ የአይሁድ ጠላት ለሆነው ለአጋጋዊው ለሐመዳቱ ልጅ ለሐማ ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ንጉሡም ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፥ ለአይሁድም ጠላት ለአጋጋዊው ለሐመዳቱ ልጅ ለሐማ ሰጠው።

参见章节 复制




አስቴር 3:10
7 交叉引用  

ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ የሃመዳታ ልጅ የሆነውን አጋጋዊውን ሐማንን ከሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በላይ ክብሩን በማስበለጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው።


ንጉሡም “እነሆ ሕዝቡ ከነንብረታቸው የአንተ ስለ ሆኑ በእነርሱ ላይ የወደድከውን አድርግ” ሲል ፈቀደለት።


ንጉሥ ሆይ! ይህ ሕዝብ በሞት የሚቀጣበትን ዐዋጅ ለማስተላለፍ መልካም ፈቃድህ ይሁን፤ ይህን ብታደርግ እኔ ለንጉሠ ነገሥት መንግሥትህ አስተዳደር መርጃ ይሆን ዘንድ ሦስት መቶ አርባ ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት ገቢ እንደማደርግ ቃል እገባለሁ።”


አስቴርም “ጠላታችንና ሞት የፈረደብንማ ሃማን የተባለው ይህ ክፉ ሰው ነው!” አለችው። ሃማንም እጅግ በመደንገጥ አንዴ ወደ ንጉሡ፥ አንዴ ወደ ንግሥቲቱ ይመለከት ነበር፤


ንጉሡም የራሱ ማኅተም ያለበትን፥ ከሃማን ጣት ወልቆ እንዲመለስ የተደረገውን ቀለበት ለመርዶክዮስ ሰጠው፤ አስቴርም መርዶክዮስን በሃማን ሀብትና ንብረት ላይ ኀላፊ አድርጋ ሾመችው።


ይሁን እንጂ የቤተ መንግሥቱ ማኅተም ያለበትና በንጉሡ ስም የተላለፈ ዐዋጅ ሊለወጥ አይችልም፤ ሆኖም እናንተ በበኩላችሁ የፈለጋችሁትን ነገር ለአይሁድ ጻፉላቸው፤ በእኔም ስም ከጻፋችሁ በኋላ የቤተ መንግሥቱን ማኅተም አትሙበት።”


跟着我们:

广告


广告