Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ንጉሡም ከሌሎቹ ልጃገረዶች ሁሉ አስበልጦ ወደዳት፤ ከሌሎቹም ሁሉ ይበልጥ በፊቱ ሞገስንና መወደድን አገኘች፤ እርሱም መንግሥታዊውን ዘውድ አንሥቶ በራስዋ ላይ ደፋላትና በአስጢን ቦታ አነገሣት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ከሌሎቹ ሴቶች ሁሉ ይበልጥ አስቴርን ወደዳት፤ ከሌሎቹ ደናግልም ሁሉ ይልቅ በርሱ ዘንድ ሞገስንና መወደድን አገኘች። ስለዚህ የእቴጌነት ዘውድ በራሷ ላይ ጫነላት፤ በአስጢንም ፈንታ ንግሥት አደረጋት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ንጉሡም ከሴቶች ሁሉ ይልቅ አስቴርን ወደደ፥ በዓይኑም ከደናግል ሁሉ ይልቅ ሞገስንና መወደድን አገኘች፥ የመንግሥቱንም ዘውድ በራስዋ ላይ አደረገ፥ በአስጢንም ፋንታ አነገሣት።

参见章节 复制




አስቴር 2:17
10 交叉引用  

“ንግሥት አስጢን ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳና ዘውድ ጭና ወደዚህ እንድትመጣ አድርጉ” አላቸው፤ ንጉሡ ይህንን ያደረገበት ምክንያት ንግሥት አስጢን እጅግ የተዋበች ስለ ነበረች ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖችና ለእንግዶቹ ሁሉ እንድትታይ ፈልጎ ነበር።


ስለዚህም አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ቴቤት ተብሎ በሚጠራው በዐሥረኛው ወር አስቴር ወደ ቤተ መንግሥቱ ተወሰደች።


እንደዚህ ባለ ጊዜ ችላ ብለሽ ዝም ብትዪ፥ ለአይሁድ ከሌላ ቦታ ርዳታ መምጣቱ አይቀርም፤ እነርሱም በእርግጥ ይድናሉ፤ አንቺ ግን ትሞቻለሽ፤ የአባትሽም የቤተሰብ ሐረግ ተቋርጦ ይቀራል፤ ነገር ግን አንቺ ንግሥት የሆንሽው በዚህ መከራ ጊዜ እኛን ለመታደግ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱንም እንደ ወራጅ ውሃ ወደ ፈቀደው ይመራዋል። የንጉሥንም አእምሮ ይቈጣጠራል።


በምድሪቱ ያሉ ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ ረጃጅም ዛፎችን አሳጥራለሁ፤ አጫጭር ዛፎችንም ከፍ ብለው እንዲያድጉ አደርጋለሁ፤ እኔ ለምለም ዛፎችን አደርቃለሁ፤ ደረቅ ዛፎችንም አለመልማለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አደርጋለሁ ያልኩትንም ሁሉ እፈጽማለሁ።”


እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።


跟着我们:

广告


广告