Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከእንግዲህ ወዲህ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ የምትኖር ማንኛዋም ሴት፥ ንግሥት አስጢን ያደረገችውን ሁሉ ስትሰማ ባልዋን በንቀት ዐይን መመልከት ትጀምራለች፤ እነርሱም በበኩላቸው ‘ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስጢንን ወደ እርሱ እንድትመጣ ቢያስጠራት እምቢ ብላው ቀርታ የለምን?’ ይላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይህ የንግሥቲቱ አድራጎት በሌሎቹ ሁሉ ዘንድ ስለሚሰማ፣ ባሎቻቸውን ይንቃሉ፤ ‘ንጉሥ ጠረክሲስ ንግሥት አስጢን ወደ እርሱ እንድትመጣ ቢያዛትም፣ እርሷ ግን መሄድ አልፈለገችም’ ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ይህ የንግሥቲቱ ነገር ወደ ሴቶች ሁሉ ይደርሳልና፦ ንጉሡ አርጤክስስ ንግሥቲቱ አስጢን ወደ እርሱ ትገባ ዘንድ አዘዘ፥ እርስዋ ግን አልገባችም ተብሎ በተነገረ ጊዜ ባሎቻቸው በዓይናቸው ዘንድ የተናቁ ይሆናሉ።

参见章节 复制




አስቴር 1:17
5 交叉引用  

ታቦቱን ይዘው ወደ ከተማ በሚገቡበት ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት እየዘለለ ሲያሸበሽብ አይታም በልብዋ ናቀችው፤


ይልቁንም አርጤክስስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን መጀመሪያ ላይ፥ ጠላቶቻቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ይኖሩ በነበሩት እስራኤላውያን ላይ በጽሑፍ የተቀናበረ ክስ መሠረቱባቸው።


ከዚህ በኋላ ከአማካሪዎቹ አንዱ የሆነው መሙካን እንዲህ ሲል የውሳኔ ሐሳብ አቀረበ፤ “በመሠረቱ ንግሥት አስጢን ያዋረደችው ንጉሡን ብቻ ሳይሆን ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖችና እንዲያውም በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ጭምር ነው።


የፋርስና የሜዶን መንግሥት ባለሥልጣኖች ሚስቶች ይህን ንግሥቲቱ የፈጸመችውን አሳፋሪ ድርጊት በሚሰሙበት ጊዜ ዛሬውኑ ፀሐይ ሳትጠልቅ በባሎቻቸው ላይ መዘባነን ይጀምራሉ፤ በየሀገሩ የሚገኙ ሚስቶችም ባሎቻቸውን ማክበርን ይተዋሉ፤ ባሎችም ከሚስቶቻቸው ጋር መጣላት ሊኖርባቸው ነው።


ነገር ግን ይህ ነገር እናንተንም ይመለከታል፤ ስለዚህ ባል ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።


跟着我们:

广告


广告