Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 1:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ ከአማካሪዎቹ አንዱ የሆነው መሙካን እንዲህ ሲል የውሳኔ ሐሳብ አቀረበ፤ “በመሠረቱ ንግሥት አስጢን ያዋረደችው ንጉሡን ብቻ ሳይሆን ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖችና እንዲያውም በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ጭምር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም ምሙካ በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንግሥት አስጢን የበደለችው ንጉሡን ብቻ ሳይሆን፣ መኳንንቱን ሁሉና በመላው የንጉሥ ጠረክሲስ አውራጃዎች የሚኖሩትን ሕዝቦች ጭምር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ምሙካንም በንጉሡና በአዛውንቱ ፊት እንዲህ አለ፦ ንግሥቲቱ አስጢን አዛውንቱን ሁሉና በንጉሡ በአርጤክስስ አገር ያሉትን አሕዛብ ሁሉ በድላለች እንጂ ንጉሡን ብቻ የበደለች አይደለችም።

参见章节 复制




አስቴር 1:16
6 交叉引用  

ይልቁንም አርጤክስስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን መጀመሪያ ላይ፥ ጠላቶቻቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ይኖሩ በነበሩት እስራኤላውያን ላይ በጽሑፍ የተቀናበረ ክስ መሠረቱባቸው።


ንጉሡም እነዚህን አማካሪዎች “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስጢንን ያመጡ ዘንድ በማዘዝ አገልጋዮቼን ብልክባት እርስዋ እምቢ ብላ ቀርታለች! ታዲያ፥ በእርስዋ ላይ መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ሕጉ ምን ይላል?” ሲል ጠየቃቸው።


ከእንግዲህ ወዲህ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ የምትኖር ማንኛዋም ሴት፥ ንግሥት አስጢን ያደረገችውን ሁሉ ስትሰማ ባልዋን በንቀት ዐይን መመልከት ትጀምራለች፤ እነርሱም በበኩላቸው ‘ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስጢንን ወደ እርሱ እንድትመጣ ቢያስጠራት እምቢ ብላው ቀርታ የለምን?’ ይላሉ።


ጳውሎስ መልስ ለመስጠት ተዘጋጅቶ ሳለ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የአይሁድ ወገኖች! በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞባችሁ ቢሆን ኖሮ ክሳችሁን በትዕግሥት በሰማሁ ነበር፤


ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “እነሆ! እኔ ልፋረድበት በሚገባኝ በሮም ንጉሠ ነገሥት የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተም በደንብ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤


跟着我们:

广告


广告