Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ግብዣው በተጀመረ በሰባተኛው ቀን ንጉሥ አርጤክስስ በወይን ጠጅ ረክቶ ደስ ባለው ጊዜ መሁማን፥ ቢዝታ፥ ሐርቦና፥ ቢግታ፥ አባግታ፥ ዜታርና ካርካስ ተብለው የሚጠሩትን ጃንደረቦች የሆኑትን ሰባቱን የእልፍኝ አገልጋዮቹን ወደ እርሱ ጠርቶ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በሰባተኛው ቀን ንጉሥ ጠረክሲስ ከወይን ጠጁ የተነሣ ደስ ስለ ተሠኘ፣ አገልጋዮቹ የሆኑትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፣ ባዛንን፣ ሐርቦናን፣ ገበታን፣ ዘቶልያንን፣ ዜታርንና ከርከስን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10-11 በሰባተኛውም ቀን ንጉሡ አርጤክስስ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ደስ ባለው ጊዜ፥ ንግሥቲቱ አስጢን መልከ መልካም ነበረችና ውበትዋ ለአሕዛብና ለአለቆች እንዲታይ የመንግሥቱን ዘውድ ጭነው ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥ ዜታርን፥ ከርከስን አዘዛቸው።

参见章节 复制




አስቴር 1:10
16 交叉引用  

ለዮሴፍ ከቀረበለት ምግብ እየተወሰደ ይሰጣቸው ነበር፤ ለብንያም ግን ከሌሎቹ አምስት እጥፍ ተሰጠው፤ በዚህ ዐይነት ከዮሴፍ ጋር እስኪጠግቡ በልተው ጠጥተው ተደሰቱ።


አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው።


ይህ በዚህ እንዳለ ንግሥት አስጢን ደግሞ በበኲልዋ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ለሴት ወይዛዝርት ግብዣ አድርጋ ነበር።


በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።


ከእነርሱም አንዱ ሐርቦና የተባለው ጃንደረባ “ንጉሥ ሆይ! ሃማን እኮ ከዚህ ሁሉ አልፎ አንተን ከሞት ያዳነህን መርዶክዮስን በስቅላት ሞት ለመቅጣት አስቦ የተከለው እንጨት በቤቱ ይገኛል፤ የእንጨቱም ርዝመት ኻያ ሁለት ሜትር ነው!” ሲል ተናገረ። ንጉሡም “ሃማንን ወስዳችሁ በዚያ እንጨት ላይ ስቀሉት!” ሲል ትእዛዝ ሰጠ።


ወይን ጠጅ ፌዘኛ፥ ጠንካራ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋሉ፤ በእነርሱ ሱስ የተጠመደ ጥበበኛ ሊሆን አይችልም።


“ልሙኤል ሆይ! ነገሥታት ወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ፥ መሳፍንትም ጠንካራ መጠጥን ለመጠጣት ይጓጉ ዘንድ ተገቢ አይደለም።


በምግብና በወይን ጠጅ ተድላ ደስታ ይገኛል፤ ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ያለ ገንዘብ አይገኝም።


ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ እንዲጫወትልን ሶምሶንን ጥሩት አሉ ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፤ በፊታቸውም ተጫወተ፤ በምሰሶና በምሰሶ መካከል አቆሙት።


ስለዚህ ሁለቱ ሰዎች ተቀምጠው አብረው ተመገቡ፤ የሴቲቱም አባት ሌዋዊውን “እባክህ ዛሬ ደስ ብሎህ እዚሁ ዕደር” አለው።


ቦዔዝ ከበላና ከጠጣ በኋላ ደስ ብሎት ነበር፤ ወደ ገብሱም ክምር ሄዶ ጋደም አለና አንቀላፋ፤ ሩትም በቀስታ ወደ እርሱ ተጠጋች፤ ልብሱንም ገለጥ አድርጋ በእግሩ አጠገብ ተኛች።


跟着我们:

广告


广告