Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤፌሶን 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ባልም የሚስቱ ራስ ነው፤ ደግሞም ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን አዳኝዋ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ክርስቶስ፣ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደሆነ ባል የሚስት ራስ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ክር​ስ​ቶስ አካሉ ለሆ​ነ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስዋ አዳ​ኝ​ዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

参见章节 复制




ኤፌሶን 5:23
11 交叉引用  

መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


“ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም።


ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን በሁሉም ነገር ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ እናድጋለን።


ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትታዘዝ እንዲሁም ሚስቶች በሁሉ ነገር ለባሎቻቸው ይታዘዙ።


እርሱ አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ በሁሉ ነገር ቀዳሚ እንዲሆን፤ ከሞት በመነሣትም ፊተኛና መጀመሪያ ነው።


እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።


የበጉ ሠርግ ስለ ደረሰና የእርሱም ሙሽራ ስለ ተዘጋጀች ኑ ደስ ይበለን! ደስታም እናድርግ! እናክብረውም!


አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤


跟着我们:

广告


广告