Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤፌሶን 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህም፦ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ብዙ ምርኮኞችን ይዞ ሄደ፤ ለሰዎችም ስጦታዎችን ሰጠ” እንደ ተባለው ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህም እንዲህ ይላል፤ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ፣ ምርኮን ማረከ፤ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ፤ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ፤” ይላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋ​ህ​ንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ፦ ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል።

参见章节 复制




ኤፌሶን 4:8
7 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ስለ አስቴር ክብር ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ጠራ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በሚገኙት አገሮች ሁሉ የደስታ በዓል እንዲደረግ ዐወጀ፤ ለጋስነት የተሞላበት ንጉሣዊ ስጦታም አደረገ።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።


ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤


እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።


ኀይሎችንና ባለሥልጣኖችን በመስቀሉ ድል ነሥቶ ትጥቃቸውን ካስፈታ በኋላ ምርኮኞች ሆነው በይፋ እንዲታዩ አደረጋቸው።


ዲቦራ ሆይ! ንቂ! ንቂ! ንቂ! መዝሙርም ዘምሪ! የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ሆይ! ተነሣ! ምርኮህንም እየመራህ ወደ ፊት ገሥግሥ!


ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ ከምርኮው ከፊሉን ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች ላከላቸው፤ ከላከላቸውም ምርኮ ጋር “ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ተወስዶ የተላከላችሁ ስጦታ ነው” የሚል መልእክት ነበር፤


跟着我们:

广告


广告