Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤፌሶን 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የክርስቶስ በመሆናችንና በእርሱ በማመናችን በእግዚአብሔር ፊት በድፍረትና በመተማመን መቅረብ እንችላለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በርሱና በርሱ ላይ ባለን እምነት አማካይነት፣ በነጻነትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በእርሱም ባለን እምነት አማካኝነት በድፍረትና በመተማመን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እኛ ጸጋ​ንና ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ በሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ​ሚ​ገ​ኘው ተስ​ፋም ያደ​ረ​ሰ​በት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን።

参见章节 复制




ኤፌሶን 3:12
12 交叉引用  

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።


ስለዚህ እግዚአብሔር ምንም ልዩነት ሳያደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ጽድቅን ይሰጣል።


ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።


ይህን የምንልበት ምክንያት በክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሔር ላይ እምነት ስላለን ነው።


በእርሱ አማካይነት ሁላችንም በአንድ መንፈስ ተመርተን ወደ አብ እንቀርባለን።


እንግዲህ፥ ታላቅ ሽልማት የምታገኙበትን መተማመኛችሁን አትጣሉት።


ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።


ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


እንግዲህ ልጆቼ ሆይ! እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ ሳንፈራ በድፍረት እንድናየውና በሚመጣበት ቀን በፊቱ እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፤


ወዳጆች ሆይ፥ ልባችን የማይወቅሰን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ሙሉ መተማመን ይኖረናል።


跟着我们:

广告


广告