መክብብ 5:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13-14 በዚህ ዓለም እጅግ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ደግሞ አየሁ፤ ይኸውም ሰዎች ለክፉ ቀን ይጠቅመናል ብለው ሀብት ያከማቻሉ፤ ነገር ግን በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ሀብታቸውን ያጡና ለልጆቻቸው የሚተላለፍ ምንም ነገር ሳይተርፋቸው ይቀራል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ከፀሓይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፦ ይህም ለባለቤቱ ጕዳት የተከማቸ ሀብት፣ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ያችም ሀብት በክፉ ነገር ትጠፋለች፥ ልጅንም ቢወልድ በእጁ ምንም የለውም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ደዌ አለ፤ ለመከራው በባለቤቱ ዘንድ የተቈጠበች ባለጠግነት ናት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ከፀሐይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፥ ለመከራው በባለቤቱ ዘንድ የተቈጠበች ባለጠግነት ናት። 参见章节 |