Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 6:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር አምላካችን እነዚህን ደንቦች እንድንፈጽምና እርሱንም እንድንፈራው አዞናል፤ እኛም ይህን ብናደርግ እርሱ ዘወትር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንልን ያደርጋል፤ ዛሬ እንደሚያደርገውም ሁሉ በሕይወት ያኖረናል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ምን ጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንም እግዚአብሔርን እንድንፈራ እግዚአብሔር አዘዘን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ዛሬም በሕይወት እንዳኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን ጌታን እንድንፈራ፥ እነዚህንም ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽም ጌታ አዘዘን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እንደ ዛሬም በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ያ​ኖ​ረን፥ ሁል​ጊ​ዜም መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ፈራ ዘንድ፥ ይህ​ች​ንም ሥር​ዐት ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዘ​ዘን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን።

参见章节 复制




ዘዳግም 6:24
20 交叉引用  

እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ በሕይወትም ያኖራቸዋል፤ በምድር ላይ ይባርካቸዋል፤ ለጠላቶቻቸውም አሳልፎ አይሰጣቸውም።


ታመውም በተኙበት አልጋ ላይ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤ ጤንነታቸውንም ይመልስላቸዋል።


እርሱ በሕይወት ጠብቆናል፤ እንድንወድቅም አላደረገም።


ሙሴም “አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ወደ እናንተ የመጣው ሊፈትናችሁና እርሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት ርቃችሁ እንድትኖሩ ነው” ሲል መለሰላቸው።


እግዚአብሔርን መፍራትና ትሑት መሆን ሀብት፥ ክብርና ሕይወትን ያስገኛል።


ጥበብ ቢኖርህ ጥቅሙ ለራስህ ነው፤ ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ራስህን ነው።


ሁሉ ነገር ስለሚሳካላቸውና የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ጻድቃንን የተባረካችሁ ናችሁ በሉአቸው።


አንድ ዓላማ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ይኸውም ለእነርሱና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካም ነገር እንዲሆንላቸው ዘወትር ያከብሩኝ ዘንድ ነው።


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ እንግዲህ አንተም ይህን አድርግ! የዘለዓለም ሕይወትንም ታገኛለህ” አለው።


ሕግን በመከተል ስለሚገኘው ጽድቅ ሙሴ የጻፈው “ሕግን የሚፈጽም ሁሉ በሕይወት ይኖራል” የሚል ነው።


ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።


እናንተ ግን ለእግዚአብሔር አምላካችሁ ታማኞች በመሆን ስለ ጸናችሁ ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት ትኖራላችሁ።


በዚያች ምድር ለረጅም ዘመናት መኖር እንድትችሉ አንተና ልጆችህ፥ የልጅ ልጆችህም በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራትና እኔ ለሰጠኋችሁ ደንቦችና ትእዛዞች ታዛዦች መሆን ይገባችኋል።


ያወርሳቸው ዘንድ ለቀድሞ አባቶቻችን በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ወደዚህ አምጥቶ ይህችን ምድር ሊሰጠን ከግብጽ ነጻ አወጣን።


“በሕይወት መኖር እንድትችሉ፥ ቊጥራችሁ እንዲበዛ፥ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውን ምድር ለመውረስ እንድትበቁ፥ ዛሬ እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዝ ሁሉ በታማኝነት ጠብቁ።


በራብ እንድትሠቃይ አደረገህ፤ ቀጥሎም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ የማታውቁትን መና አበላህ፤ ይህንንም ማድረጉ ሰው ሕይወቱ ተጠብቆለት መኖር የሚችለው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አለመሆኑን ሊያስተምርህ ነው።


跟着我们:

广告


广告