Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 5:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እንዲህ አላችሁ፦ ‘በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር በሰማነው ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ታላቅነቱንና ክብሩን በግልጥ አሳይቶናል፤ እግዚአብሔር ካነጋገረው በኋላ እንኳ ሰው በሕይወት መኖር እንደሚችል በዛሬው ዕለት አይተናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እንዲህም አላችሁ፤ “አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ግርማውን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እግዚአብሔር አነጋግሮትም እንኳ፣ ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እንዲህም አላችሁ፦ ‘እነሆ፥ አምላካችን ጌታ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔር ከሰው ተነጋግሮ ሰውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አላ​ች​ሁም፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሩ​ንና ታላ​ቅ​ነ​ቱን አሳ​ይ​ቶ​ናል፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ድም​ፁን ሰም​ተ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰው ጋር ሲነ​ጋ​ገር፥ ሰው​ዬው በሕ​ይ​ወት ሲኖር ዛሬ አይ​ተ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውዬውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።

参见章节 复制




ዘዳግም 5:24
12 交叉引用  

ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው።


ያዕቆብ ከጵንኤል ተነሥቶ ሲሄድ ፀሐይ ወጥታ ነበር፤ በጭኑም ሕመም ምክንያት ያነክስ ነበር።


የእምቢልታውም ብርቱ ድምፅ እያከታተለ ማስተጋባት ቀጠለ፤ ሙሴ ሲናገር እግዚአብሔር በነጐድጓድ ይመልስለት ነበር፤


እግዚአብሔር ሙሴን ለእስራኤላውያን እንዲነግር እንዲህ ሲል አዘዘው፥ “እኔ እግዚአብሔር ከሰማይ እንዴት እንደ ተናገርኳችሁ አይታችኋል፤


ፊቴን አይቶ ለመኖር የሚችል ሰው ስለሌለ ፊቴን ለማየት አትችልም።


የሆነውን ሁሉ በዚህ ምድር ለሚኖሩት ሕዝቦች ይነግራሉ፤ እነዚህ ሕዝቦች አንተ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆንህንና ደመናህ በላያችን በረበበ ጊዜ በግልጥ እንደምትታይ፥ ቀን በደመና ዐምድ፥ ሌሊት በእሳት ዐምድ እፊት እፊታችን እየሄድክ እንደምትመራን ከሰሙ ቈይተዋል።


የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት ተናገሩ።


እናንተ በሰማችሁት ዐይነት እግዚአብሔር በእሳት ነበልባል ውስጥ ሆኖ ተናግሮት በሕይወት ለመኖር የቻለ ሕዝብ ከቶ አለን?


“ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ የነገድ አለቆችና መሪዎች ሁሉ ወደ እኔ መጥታችሁ፥


ነገር ግን ያ ብርቱ እሳት ያጠፋናል፤ ታዲያ ለምን መሞት እንፈልጋለን? እግዚአብሔር አምላካችን እንደገና ቢናገረን እንሞታለን።


ማኑሄ ሚስቱን “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጥ እንሞታለን!” አላት።


跟着我们:

广告


广告