Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 31:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የቱን ያህል ዐመፀኞችና ዐንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ ዐውቃለሁና። እኔ በሕይወት ከእናንተ ጋራ እያለሁ በእግዚአብሔር ላይ ካመፃችሁ፣ ከሞትሁ በኋላማ የቱን ያህል ልታምፁ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፤ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል፤ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?

参见章节 复制




ዘዳግም 31:27
18 交叉引用  

ለእግዚአብሔር ታዘዙ እንጂ እንደ እነርሱ ልበ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘለዓለም ወደ ቀደሰው በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ ኑ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ቊጣውን ከእናንተ እንዲመልስ እርሱን ብቻ አምልኩ፤


ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልጠበቁም፤


እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ።


እነርሱ ግን እግዚአብሔርን በመበደል ኃጢአት መሥራት ቀጠሉ፤ በበረሓም በልዑል እግዚአብሔር ላይ ዐመፁ።


እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።


“እነርሱ ዘወትር የእግዚአብሔርን መመሪያ መስማት የማይፈልጉ ዐመፀኛ ዘርና የማይታመኑ ልጆች ናቸው።


እንደማይተጣጠፍ ነሐስና እንደ ጠንካራ ብረት የማትመለሱ እልኸኞች መሆናችሁን ዐውቃለሁ።


እናንተ ግን እልኸኛና ዐመፀኛ ሕዝብ በመሆናችሁ፥ እኔን ትታችሁ ኰብልላችኋል።


“ነገር ግን ልጆቻቸው በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚፈጽመው ሁሉ ሕይወት የሚያስገኝለትን ሕጌን አፈረሱ፤ ሕጎቼንም አልጠበቁም፤ ሰንበትንም አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ሳሉ የቊጣዬን ኀይል በእነርሱ ላይ በማውረድ ሁሉንም ላጠፋቸው አስቤ ነበር።


“እናንተ እልኸኞች ልባችሁ የተደፈነ! ጆሮአችሁም የማይሰማ! እናንተም ልክ እንዳባቶቻችሁ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ።


“የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ይህን መጽሐፍ ወስዳችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ምስክር ይሆንባቸዋል።


‘ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አያለሁ፤ እነርሱ የተበላሸ ትውልድ እምነት የሚጣልባቸው ልጆች አይደሉም’ አለ።


“ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ ‘እነሆ፥ ይህ ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ እልኸኛ መሆኑን ዐውቃለሁ፤


እኔ ካወቅኋችሁ ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ ናችሁ።


“እግዚአብሔር አምላካችሁ እነርሱን ከፊታችሁ ካባረረላችሁ በኋላ ‘እግዚአብሔር ወደዚህች ምድር ያመጣን ስለ መልካም ሥራችን ነው’ ብላችሁ አታስቡ፤ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝብ ነቃቅሎ የሚያባርርልህ እነርሱ ክፉዎች ስለ ሆኑ ብቻ ነው።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባታዳምጡ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ይበረታባችኋል፤


跟着我们:

广告


广告