Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 “ጠላቶችህ ከተሞችህን ከበው በሚያስጨንቁህም ጊዜ፥ የምትበላው አጥተህ ግራ ሲገባህ እግዚአብሔር አምላክህ የሰጠህንና የሆድህ ፍሬዎች የሆኑትን ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ሥጋ ለመብላት ትገደዳለህ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 ጠላቶችህ ከብበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፣ ከሥቃይ የተነሣ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን፣ የወገብህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 “ጠላቶችህ ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፥ ከሥቃይ የተነሣ፥ ጌታ እግዚአብሔር የሰጠህን፥ የሆድህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 ጠላ​ቶ​ች​ህም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ሥጋ ትበ​ላ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:53
11 交叉引用  

ጠላት ከተማይቱን ከቦ ሕዝቡን ለመጨረስ ያስጨንቋቸዋል፤ በዚህ ጊዜ ምግብ ሁሉ አልቆ ሕዝቡ ስለሚራብ እርስ በርሳቸው ይባላሉ፤ እንዲያውም ወላጆች የልጆቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።’ ”


ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!


የርኅሩኅ ሴቶች እጆች የገዛ ልጆቻቸውን ቀቀሉ፤ ከተማዋ በተደመሰሰች ጊዜ እነዚያ የተቀቀሉ ልጆች ለሰዎች ምግብ ሆኑ።


በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።


ስለዚህም ከመራባችሁ ጽናት የተነሣ የገዛ ልጆቻችሁን ለመብላት ትገደዳላችሁ።


በዚያን ጊዜ ለነፍሰጡሮችና ለሚያጠቡ እመጫቶች ወዮላቸው!


“ልጆችህ፥ የምድርህ ፍሬ፥ የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋህ የተረገመ ይሆናል።


በመካከላችሁ በመለሳለስና በቅምጥልነት በትውልዱም በመመካት የሚኖረው ሰው እንኳ ለወንድሙ፥ ዐቅፋው ለምትተኛው ሚስቱና ከጥፋት ለተረፉት ልጆቹ ከዚያ ምግብ ለመስጠት ይሰስታል።


በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው በጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላው ነገር ስለሌለው ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለማናቸውም አይሰጥም።


በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው፥ በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው የጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላ ነገር ስለሌላት በምሥጢር ከምትበላቸው ከማሕፀንዋ ከወጡ ልጆችዋና ከእንግዴልጅዋ ለማንም አትሰጥም።


跟着我们:

广告


广告