Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 “የአንተ ኀይል እየደከመ ሲሄድ፥ በምድርህ የሚኖሩ የመጻተኞች ኀይል ግን ይበረታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 በመካከልህ የሚኖር መጻተኛ ከአንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል፣ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 “በመካከልህ የሚኖር መጻተኛ ከአንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 በአ​ንተ መካ​ከል ያለ መጻ​ተኛ በአ​ንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 በአንተ መካከል ያለ መጻተኛ በአንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አንተም ዝቅ ዝቅ ትላለህ።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:43
18 交叉引用  

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሁሉ ተዋቸው፤ ከፊቱም እስኪወገዱ ድረስ በዝባዞች ለሆኑት ጠላቶቻቸው አሳልፎ በመስጠት ቀጣቸው።


እኛ በጣም ስለ ተዋረድን በአባቶቻችን ኃጢአት ምክንያት አትቅጣን ፈጥነህም ምሕረት አድርግልን።


ከኃጢአትዋ ብዛት የተነሣ እግዚአብሔር ችግር እንዲደርስባት አደረገ፤ ጠላቶችዋ ገዢዎችዋ ሆነዋል፤ ልጆችዋም በጠላት ተማርከው ተወስደዋል ጠላቶችዋ ግን ተሳክቶላቸዋል።


እግዚአብሔር ያሰበውን ፈጸመ፤ ቀድሞ የተናገረውን ቃል ተግባራዊ አደረገ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት በወሰነው መሠረት ያለ ርኅራኄ አፈራረሰ፤ ጠላት በእናንተ ላይ ደስ እንዲሰኝ አደረገ፤ የጠላቶቻችሁንም ኀይል አበረታ።


ጲላጦስም “እናንተ ራሳችሁ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት” አላቸው። አይሁድም “እኛ ሰውን ለመግደል አልተፈቀደልንም” አሉት።


እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከሮማው ንጉሠ ነገሥት በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም!” ሲሉ መለሱለት።


አምላክህ እግዚአብሔር በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ ራስ መሪ ያደርግሃል እንጂ እንደ ጅራት ወደ ኋላ እንድትቀር አያደርግህም፤ ዛሬ እኔ የምሰጥህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በታማኝነት ብትፈጽም ምንም ዐይነት ውድቀት ሳይደርስብህ ወደፊት ትገሠግሣለህ እንጂ ወደ ኋላ አትቀርም፤


ሶምሶን ይህን እንዲያደርግ የሚመራው እግዚአብሔር እንደ ሆነ ወላጆቹ አላወቁም፤ በዚያም ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ይገዙ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን ለመቃወም ምክንያት ይፈልግ ነበር።


ስለዚህ አሁን እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ እንደማላስወጣቸው እነግራችኋለሁ፤ እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ፤ ባዕዳን አማልክታቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል።”


ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድያማውያን ምክንያት ችግር ደረሰባቸው፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።


跟着我们:

广告


广告