Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 24:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የወይራ ዛፍ ፍሬህንም አንድ ጊዜ ከለቀምክ በኋላ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ እንደገና ወደ እርሱ አትመለስ፤ እርሱን ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ፣ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የወ​ይ​ራ​ህን ፍሬ በለ​ቀ​ምህ ጊዜ ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ አጥ​ር​ተህ ለመ​ል​ቀም ዳግ​መኛ አት​መ​ለስ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የወይራህን ፍሬ ባረገፍህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ ማርገፉን ለማጣራት አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን።

参见章节 复制




ዘዳግም 24:20
4 交叉引用  

የወይን መከርህንም ስትሰበስብ በሐረጉ ላይ ተሰውሮ የቀረውን ወይም በመሬት ላይ የረገፈውን የወይን ዘለላ አጥርተህ ለመልቀም እንደገና ወደ ኋላ አትመለስ፤ ይህን ሁሉ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤


“እህልህን በምትሰበስብበት ጊዜ የረሳኸው ነዶ ቢኖር እርሱን ለማምጣት ወደ ኋላ አትመለስ፤ እርሱ ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው መበለቶች ይቅርላቸው፤ ይህን ብታደርግ በምትሠራው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክሃል።


የወይንህንም ዘለላ በምትሰበስብበት ጊዜ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ ወደ ወይኑ ሐረግ ዳግመኛ አትመለስ፤ የቀሩትን ዘለላዎች ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው።


跟着我们:

广告


广告