ዘዳግም 20:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ‘የእስራኤል ሰዎች ሆይ! አድምጡ! እነሆ፥ ዛሬ ወደ ጦርነት መሄዳችሁ ነው፤ ከጠላቶቻችሁ የተነሣ አትፍሩ! ወኔአችሁ አይቀዝቅዝ፤ አትሸበሩም! 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እንዲህም ይበል፤ “እስራኤል ሆይ ስማ፤ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው፤ ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እንዲህም ይበል፦ ‘እስራኤል ሆይ ስማ፤ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው፤ ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ዛሬ ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ትሄዳላችሁ፤ ልባችሁ አይታወክ፤ አትፍሩ፤ አትሸበሩ፤ ከፊታቸውም ፈቀቅ አትበሉ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፤ ዛሬ ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ትቀርባላችሁ፤ ልባችሁ አይታወክ፥ አትፍሩ፥ አትንቀጥቀጡ፥ በፊታቸውም አትደንግጡ፤ 参见章节 |