Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 2:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን በእኛ እጅ ስለ ጣለው እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ሰው ሁሉ ገደልን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 አምላካችን እግዚአብሔር በእጃችን ላይ ጣለው፤ እኛም፣ እርሱን ከወንድ ልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድ ላይ መታነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ጌታ አምላካችንም እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አም​ላ​ካ​ች​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን፤ እር​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ መታን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንም ልጆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ መታን።

参见章节 复制




ዘዳግም 2:33
14 交叉引用  

በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።


የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ገደለ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


የምድርህንም ወሰን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳው እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንዲሰፋ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁ፤ ከፊትህም ታሳድዳቸዋለህ።


እስራኤላውያን ግን ድል ነሡአቸው፤ ከአርኖን ወንዝ አንሥቶ በስተሰሜን እስከ ዐሞናውያን ወሰን ማለትም እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ የሚገኘውን ግዛት ያዙ፤ ይሁን እንጂ የዐሞናውያን ወሰን በብርቱ የተጠበቀ በመሆኑ ወደዚያ አልገቡም።


ንጉሥ ሲሖንም ያለውን ሰው ሁሉ አሰልፎ በያሐጽ ከተማ አጠገብ ከእኛ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤


“እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን ከተማዎች በጦርነት በምትይዝበት ጊዜ ግን በውስጣቸው የሚገኘውን ሰው ሁሉ ግደል።


አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቁ ዘንድ እንጀራ አልበላችሁም ወይን ወይም ጠንካራ መጠጥ አልጠጣችሁም።


እግዚአብሔር አምላክህ እነዚህን ሁሉ ሕዝቦች ለእናንተ አሳልፎ ሲሰጣቸውና እነርሱን ድል በምትነሣበት ጊዜ ሁሉንም መደምሰስ አለብህ፤ ከእነርሱ ጋር ምንም ዐይነት ውል አታድርግ፤ አትራራላቸውም።


እግዚአብሔርም ለቀድሞ አባቶቻቸው በገባው ቃል መሠረት በአካባቢያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድልን አቀዳጅቶአቸው ስለ ነበረ ከጠላቶቻቸው አንድ እንኳ በፊታቸው ሊቆም አልቻለም።


ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ።


እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤


跟着我们:

广告


广告