ዘዳግም 2:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 “በሞአብ በኩልም ካለፍን በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለን፦ ‘አሁን ተነሥታችሁ የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ የሚገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ከነምድሩ ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ፤ እርሱን ወግታችሁ ምድሩን ውረሱ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 “አሁኑኑ ተነሡና የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ እነሆ፤ የሐሴቦንን ንጉሥ፣ አሞራዊውን ሴዎንንና አገሩን በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ፤ ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ጦርነት ግጠሙት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 “ደግሞም አለ፦ ‘ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፥ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርሷን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ። 参见章节 |