Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም ለሚኖሩት ለዔሳው ዘሮችም እንደዚሁ አድርጎላቸው ነበር፤ ይኸውም ቀድሞ የኖሩባትን ሖራውያንን ደምስሶ እስከ አሁን የሚኖሩባትን ምድራቸውን ኤዶማውያን ወርሰው እንዲሰፍሩባት አድርጎአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር ሖሪውያንን ከፊታቸው ባጠፋ ጊዜ፣ በሴይር ለሚኖሩት የዔሳው ዘሮች ያደረገው ይህንኑ ነበር። እነርሱም አሳድደው በማስወጣት ባስለቀቁት ስፍራ ላይ እስከ ዛሬ ይኖራሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ፥ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ፥ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፥ እነርሱንም ቀምተው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።

参见章节 复制




ዘዳግም 2:22
7 交叉引用  

የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በኤዶም፥ በበረሓ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ባለው ስፍራ ድል ነሡአቸው።


ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው በተራራማው አገር በኤዶም ተቀመጠ።


ሖራውያንም በኤዶም ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን የዔሳው ዘሮች ሖራውያንን ነቃቅለው በማባረር በእነርሱ ቦታ ሰፍረውበት ነበር፤ ይኸውም እስራኤላውያን ዘግየት ብለው እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ እንዳደረጉት ዐይነት መሆኑ ነው።]


እነርሱም እንደ ዐናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች፥ ብርቱና ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ዐሞናውያን ስለ ደመሰሱአቸው ምድራቸውን ወርሰው ራሳቸው ሰፍረውበት ነበር።


የኤዶምን ኮረብታማ አገር ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታኽል እንኳ አልሰጣችሁምና በእነርሱ ላይ ጦርነት አታንሡ።


跟着我们:

广告


广告