Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 2:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚህም በኋላ የሎጥ ዘሮች ወደሚኖሩበት ወደ ዐሞናውያን ምድር ትቃረባላችሁ፤ እነርሱንም አታስቸግሩአቸው፤ ወይም ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ ለእነርሱ ከሰጠኋት ምድር ለእናንተ ምንም አልሰጣችሁም።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከየትኛውም የአሞናውያን ምድር ለእናንተ ርስት ስለማልሰጣችሁ፣ አሞናውያን ዘንድ በደረሳችሁ ጊዜ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው። ያን ቦታ ርስት አድርጌ ለሎጥ ዘሮች ሰጥቻቸዋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ፥ ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና፥ አትጣላቸው አትውጋቸውም።’”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለሎ​ጥም ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከአ​ሞን ልጆች ምድር ርስት አል​ሰ​ጥ​ህ​ምና በአ​ሞን ልጆች አቅ​ራ​ቢያ ስት​ደ​ርስ አት​ጣ​ላ​ቸው፤ አት​ው​ጋ​ቸ​ውም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው አትውጋቸውም።

参见章节 复制




ዘዳግም 2:19
8 交叉引用  

“እነሆ አሁን የዐሞን፥ የሞአብና የኤዶም ሕዝቦችን ተመልከት፤ አደጋ ጥለውብናል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ወደነዚህ ሕዝቦች ግዛቶች እንዲገቡ አልፈቀድክላቸውም፤ የቀድሞ አባቶቻችን እነርሱን ዞረው አለፉ እንጂ አላጠፉአቸውም፤


ስለ ሞአብም የተነገረው ቃል ይህ ነው፤ የዔርና ቂር ከተሞች በአንድ ቀን ሌሊት ተደመሰሱ፥ የሞአብ ምድር ጭር አለች፤


ነገር ግን ወደ ዐሞናውያን ግዛት አጠገብ ወይም ወደ ያቦቅ ወንዝ ዳርቻ ወይም ወደ ኮረብታማይቱ አገር ከተሞች ወይም እግዚአብሔር እንዳንደርስባቸው ወዳዘዘን እነዚህን ከመሳሰሉት አገሮች ወደ አንዲቱ እንኳ አልቀረብንም።


የኤዶምን ኮረብታማ አገር ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታኽል እንኳ አልሰጣችሁምና በእነርሱ ላይ ጦርነት አታንሡ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ ‘የሎጥ ዘሮች የሆኑትን ሞአባውያንን አታስቸግሩ፤ ከእነርሱም ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ የዔርን ከተማ ለእነርሱ መኖሪያ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህም ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁም።’ ”


በሌላም በኩል በሓሴቦን እስከ አሞናውያን ድንበር ድረስ የነገሠውን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖንን ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል።


跟着我们:

广告


广告