Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 18:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “የቀንድ ከብት ወይም በግ በሚሠዋበት ጊዜ ካህናቱ ወርቹን፥ አገጩንና፥ ጨጓራውን ይወስዳሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኰርማ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፣ መንገጭላውንና ሆድ ዕቃውን ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “በሬ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ አገጩንናና ሆድ ዕቃውን ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሬ ወይም በግ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሕዝብ የካ​ህ​ናቱ ወግ ይህ ይሆ​ናል፤ ወር​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ጕን​ጮ​ቹን፥ ጨጓ​ራ​ው​ንም ለካ​ህኑ ይሰ​ጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሬ ወይም በግ ለመሥዋዕት ከሚያቀርቡት ሕዝብ የካህናቱ ወግ ይህ ይሆናል፤ ወርቹንና ሁለቱን ጉንጮቹን ጨጓራውንም ለካህኑ ይሰጣሉ።

参见章节 复制




ዘዳግም 18:3
7 交叉引用  

“አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።


ሕዝቤ የአንድነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የእንስሳው ፍርምባና በቀኝ በኩል ያለውን የኋላ እግር ለአሮንና ለልጆቹ ድርሻ ሆኖ እንዲመደብ ወስኛለሁ፤ ውሳኔውም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ ይህ እንግዲህ ሕዝቡ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው መባ ነው።


ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ግን ንጹሕ ስለሚሆን የእርሱ ድርሻ የሆነውን የተቀደሰ የእህል መባ መብላት ይችላል፤


“በተጨማሪም እስራኤላውያን በእኔ ፊት በመወዝወዝ የሚያቀርቡአቸው ልዩ ስጦታዎች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ እነርሱን ለአንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ ንጹሕ የሆነ ማንኛውም የቤተሰብህ አባል ሊመገባቸው ይችላል።


“እስራኤላውያን የሚሰጡኝን ምርጥ የሆነ በኲራት፥ ይኸውም የወይራ ዘይት፥ የወይን ጠጅና እህል ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።


የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን፥ ማለትም ሥጋውንና ደሙን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የሌሎች መሥዋዕቶችህ ደም ከአምላክህ ከእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን ልትበላ ትችላለህ።


跟着我们:

广告


广告