Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 7:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “እርሱም ትርጒሙን እንዲህ ሲል አስረዳኝ፤ ‘አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛ መንግሥት ነው፤ ይህ መንግሥት ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ በመሆኑ ምድርን ሁሉ በመውረር ረግጦና ቀጥቅጦ ይገዛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ‘አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛው መንግሥት ነው። ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላውንም ምድር እየረገጠና እያደቀቀ ይበላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እንዲህም አለ፦ አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፥ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል።

参见章节 复制




ዳንኤል 7:23
5 交叉引用  

እንደገናም ሁሉን ነገር የሚሰባብርና የሚያንከታክት እንደ ብረት የጠነከረ አራተኛ መንግሥት ይነሣል፤ ብረት ሁሉን ነገር ሰባብሮ እንደሚያደቅ፥ እርሱም ከእርሱ በፊት የነበሩትን መንግሥታት ሁሉ ሰባብሮ ያደቃል።


ይህም የሆነው ዘለዓለማዊው መጥቶ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ፍትሕ እስከ ሰጠበት ጊዜ ድረስ ነው፤ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወርሱበት ጊዜ ደረሰ።


ዐሥሩ ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡት ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያን በኋላ ከበፊተኞቹ ነገሥታት የተለየ ሌላ ንጉሥ ተነሥቶ ከዐሥሩ መንግሥታት ሦስቱን ይገለብጣል፤


“ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።


በዚያን ጊዜ በሮማውያን ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ እንዲቈጠሩ ከሮማው ንጉሠ ነገሥት አውግስጦስ ታወጀ።


跟着我们:

广告


广告