Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 2:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ናቡከደነፆር ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ወድቆ ለዳንኤል ሰገደለት፤ የእህል ቊርባንና ዕጣን እንዲያቀርቡለትም አዘዘ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነፆር በግንባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል ሰገደለት፤ አከበረውም፤ መሥዋዕትና ዕጣንም እንዲያቀርቡለት አዘዘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር በግምባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል ሰገደለት፥ የእህሉንም ቁርባን ዕጣኑንም ያቀርቡለት ዘንድ አዘዘ።

参见章节 复制




ዳንኤል 2:46
12 交叉引用  

ይህም ሁሉ የሚሆንበት ምክንያት የሰማይ አምላክ በደስታ የሚቀበለውን መሥዋዕት ሁሉ በማቅረብ ለእኔና ለልጆቼ ሕይወት እንዲጸልዩልን ነው፤


የመለከት የእንቢልታ የመሰንቆ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንት፥ የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ በምድር ላይ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል እንድትሰግዱ ታዛችኋል።


ስለዚህ ወገኖች፥ ከልዩ ልዩ ሀገር የመጡ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ሁሉ የመለከትና፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆና፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ በመሬት ላይ ተደፍተው ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ሰገዱ።


ገብርኤልም መጥቶ በአጠገቤ በቆመ ጊዜ ደንግጬ ወደ መሬት ወደቅኹ። እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! ራእዩ የሚያመለክተው ስለ ዓለም መጨረሻ መሆኑን ተረዳ” አለኝ።


ከተሞቻችሁንም ውድማ አደርጋለሁ የማምለኪያ ስፍራዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ መሥዋዕታችሁንም አልቀበልም።


ኢየሱስንም እያመሰገነ በእግሩ ሥር በግምባሩ ተደፋ፤ እርሱ የሰማርያ ሰው ነበር።


ጴጥሮስ ወደ ቤት ሲገባ ቆርኔሌዎስ ወደ እርሱ ቀረበና በእግሩ ሥር ወድቆ ሰገደለት።


ከከተማው ውጪ ያለው የድያ ቤተ መቅደስ ካህን ኮርማዎችንና የአበባ ጒንጒኖችን ወደ ከተማው በር አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ለጳውሎስና ለበርናባስ መሥዋዕት ሊያቀርብላቸው ፈለገ።


ሰዎቹም “ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል፤ ወይም በድንገት ሞቶ ይወድቃል” በማለት ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም ጒዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ አሳባቸውን ለወጡና “ይህስ አምላክ ነው!” አሉ።


በእግዚአብሔር ፊት በዙፋኖቻቸው ላይ የተቀመጡት ኻያ አራቱ ሽማግሌዎችም በግንባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤


እኔም ለመልአኩ ልሰግድለት በእግሩ ሥር በግንባሬ ተደፋሁ፤ እርሱ ግን “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክርነት ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ! የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ ነው” አለኝ።


እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ፤ እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ልሰግድለት በእግሩ ሥር ወደቅኩ።


跟着我们:

广告


广告