42 ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ በሚያንሰራፋበትም ጊዜ ግብጽም ራስዋ አታመልጥም።
42 ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል፤ ግብጽም አታመልጥም።
42 እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብጽም ምድር አታመልጥም።
በቀድሞ መኖሪያቸው በደቡብ ግብጽ በጳጥሮስ እንዲኖሩ እፈቅድላቸዋለሁ፤ በዚያም ደካማ መንግሥት ይሆናሉ፤
ውብ የሆነችውንም የተስፋይቱን ምድር ይወራል፤ ብዙ አገሮችም በእርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ ነገር ግን የኤዶም፤ የሞአብና የዐሞን አገሮች ከወረራው ያመልጣሉ።
የግብጽን ወርቅ፤ ብርና ሌላውንም የከበረ ነገር ሁሉ ከተደበቀበት ቦታ ይወስዳል፤ ሊቢያንና ኢትዮጵያንም ድል ያደርጋል፤
ለንጉሡ ለሠራዊት አምላክ የማይሰግዱለት ሕዝቦች ቢኖሩ በምድራቸው ዝናብ አይዘንብላቸውም።
ሬሳቸውም በምሳሌያዊ አጠራር ሰዶም ወይም ግብጽ በምትባል በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይጋደማል፤ ይህች ከተማ የእነርሱ ጌታ የተሰቀለባት ናት።