Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ቈላስይስ 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እነዚህ ሁሉ በሰው ሠራሽ ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ ሥራ ላይ ከዋሉ በኋላ ለመጥፋት የተወሰኑ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ ጠፊ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እነዚህ ሁሉ ትእዛዛት በጥቅም ላይ በመዋላቸው የሚጠፉትን ነገሮች የሚጠቁሙ ናቸው፤ እንዲያው በቀላሉ የሰው ትእዛዛትና አስተምሮ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ይህ ሁሉ እንደ ሰው ትእ​ዛ​ዝና ትም​ህ​ርት ለጥ​ፋት ነውና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት፦ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና።

参见章节 复制




ቈላስይስ 2:22
12 交叉引用  

ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።


ደንቆሮዎች የሚነበብላቸውን መጽሐፍ መስማት የሚችሉበት ጊዜና በጨለማ የሚኖሩ ዕውሮችም ዐይኖቻቸው በርተው የሚያዩበት ጊዜ ይመጣል።


ንጉሡ የቀድሞ አባቶቹን አማልክት ያቃልላል፤ ሴቶች የሚወዱአቸውንም አማልክት ይንቃል፤ እርሱ ራሱን ከሁሉ በላይ አድርጎ ስለሚቈጥር አማልክትን ሁሉ ችላ ይላል።


ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”


“ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም።


ትእዛዞቹም “አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ” የሚሉ ናቸው።


የአይሁድን ተረት እንዳይከተሉና እውነትን የሚቃወሙትን ሰዎች ትእዛዝ እንዳይሰሙ በብርቱ ገሥጻቸው።


እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ይሳደባሉ፤ እነርሱ ለመጠመድና ለመገደል እንደ ተወለዱ፥ በተፈጥሮ ስሜት እንደሚኖሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው፤ እንስሶች እንደሚጠፉ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።


“ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”


跟着我们:

广告


广告